Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየሰባት አንጋፋና ታዋቂ ሠዓሊያን ዓውደ ርዕይ ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል

የሰባት አንጋፋና ታዋቂ ሠዓሊያን ዓውደ ርዕይ ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል

ቀን:

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ከግንባር ቀደምቱ ተርታ የሚሠለፉ ሰባት አንጋፋ ሠዓሊያን ሥራዎቻቸው የሚቀርብበት ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ አብራክ የሥነ ጥበብ ማዕከል ሐሙስ ኅዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ይከፈታል።

አብራክ የሥነ ጥበብ ማዕከል ከትናንት በስቲያ ኅዳር 12 ቀን በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ ሠዓሊያኑ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1960ዎቹ መጨረሻ በዓለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የተመረቁ፣ ባህር ማዶ ዘልቀው ከፍተኛ ትምህርት የተከታተሉ፣ ከፊሎቹም በትምህርት ቤቱ ላይ በማስተማር ላይ የሚገኙ ናቸው።

በአብራክ ማዕከል ሠላሳ አራት ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡት ሠዓሊያን አብዱራህማን መሐመድ ሸሪፍ፣ ወርቁ ጎሹ፣ ዘሪሁን የትምጌታ፣ ደስታ ሐጎስ፣ ቱሉ ጉያ፣ ጥበበ ተርፋና ልዑልሰገድ ረታ ናቸው።

በኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያኖሩና ለዘርፉም በርካታ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆናቸውንም በወቅቱ ተገልጿል፡፡

ሰባቱ ሠዓሊያን ከ1956 ዓ.ም. እስከ 1969 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ጊዜያት ውስጥ የተመረቁ ሠዓሊዎች መሆናቸውን የገለጹት በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህር ገረመው ፈይሳ (ዶ/ር) እነዚህም ሠዓሊዎችን ለሥዕል ዓውደ ርዕዩ ሲመረጡ በቂ የሆነ ጥናት ተደርጎ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዓውደ ርዕዩ የተዘጋጀው አንጋፋዎቹን ባለውለታ ሠዓሊዎችንና ሥራዎቻቸውን ለአሁኑ ትውልድ ለማስተዋወቅ እንደሆነ የገለጹት የሥነ ጥበብ ማዕከሉ የቦርድ አባል ወ/ሮ ዓይናለም እምሩ ናቸው፡፡ አያይዘውም ጋለሪዎች የሥዕሎች መሸጫ ብቻ ሳይሆኑ ማሳያም እንደሆኑ ለማስገንዘብ እንደሆነም ገልጸዋል።

በጊዜ ሒደትም የአብራክ የሥነ ጥበብ ማዕከልን ወደ ትልቅ የሥነ ጥበብ ማሳያ በመቀየር የሙዚየም ሚና ያለው ማዕከል ለማድረግ መታሰቡንም ሳይጠቅሱ አላለፉም።

ለሁለት ሳምንታት የየሚቆየው ዓውደ ርዕዩ ከተጠናቀቀ በኋላ በቋሚነት የሥዕል ጋለሪ የሚሠራ መሆኑን፣ እንዲህ ዓይነት የሥዕል ጋላሪዎችን በመክፈትም የኪነ ጥበብ ዘርፉን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ ዓይናለም ጠቁመዋል፡፡

የሰባቱን ሠዓሊዎች ሥራ የሚሳየው መጽሔት በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በስፓኒሽ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ መታተሙ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...