Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ300 ሺሕ በላይ ወገኖችን የማገዝ ትልም

በበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ300 ሺሕ በላይ ወገኖችን የማገዝ ትልም

ቀን:

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ እንደነበር ባህላዊና ሃይማኖታዊ ተግባራት ምስከር ናቸው፡፡

ማኅበረሰባዊ ውቅሩ በራሱ ከመረዳዳትና ከመተጋገዝ ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኑሯቸው ነው ማለት ያስችላል፡፡

ሰው ሲታመም ማስታመም፣ አደጋ ሲደርስ ማሳከም፣ ልጅ ሲወለድ ተሰብስቦ መደገፍና ሌሎችም በርካታ በጎ ተግባራት ኢትዮጵያውያን ይከውኑታል፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት  በኢትዮጰያ ይደረጉ የነበሩ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችም ልማታዊ ሥራዎችን ከማስፋፋት አንፃር አስተዋጽኦ ነበራቸው። በአብዛኛው የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትና በመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ነበር።

የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ሥምሪትን በተደራጀ አግባብ በ2003 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ አገልግሎቱ የክረምትና በየበጋ በሚሉ ክፍሎች በተለያዩ መስኮች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 

ከ2010 ዓ.ም. የክረምት ወራት ጀምሮ እጅግ በተለየ መንገድ በፖሊሲ የሚመራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት  ዘመቻዎች ተጀምረዋል። የአረጋውያንን ቤቶች በመጠገን፣ ችግረኛ ተማሪዎችን በመርዳት፣ ደም በመለገስ  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች፣ ሌሎች የማኅበረሰቡ ክፍሎችም ተከትለው ለማስፋፋት ጥረዋል፡፡

ከሰኔ 2014 እስከ መስከረም 2015 ዓ.ም. ‹‹በጎነት ለዘላቂ አብሮነት›› በሚል መሪ ሐሳብ የተካሄደው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መከናወኑን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የዘንድሮ የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ደግሞ ‹‹በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበራዊ መስተጋብር›› በሚል መሪ ቃል በሰባት መርሐ ግብሮችና በ15 ንዑሳን ተግባራት እንደሚከናወኑ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ከሚቆየው የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሮቹ መካከል ሰብዓዊና ማኅበራዊ፣ የወሰንና የድንበር የለሽ አገልግሎት ጤና ለሁሉም፣ በጎነት በትምህርት ቤት፣ እንዲሁም አረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ይገኙበታል፡፡

ከንዑሳን ተግባራት አንዱ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ነው፡፡ 24,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ የሦስት ሺሕ አቅመ ደካሞችን የአረጋውያንን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ የአገር ባለውለታዎችንና እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ቤቶች ለማደስ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

‹‹በጤና ለሁሉም›› መርሐ ግብር ውስጥ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ከፍለው መታከም ለማይችሉ 10,000 ሰዎች እንዲታከሙ ለማድረግ ኮሚሽኑ አቅዷል፡፡ በዚህ የአገልግሎት ተግባር 500 በጎ ፈቃደኛ የሕክምና ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኮሚሽኑ በልዩ ትኩረት እሠራለሁ ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል የደም ልገሳ አንዱ ነው፡፡ ኮሚሽነሩ ጀማሉ ጀንበሩ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ በሕክምና ተቋማት የሚከሰተውን የደም እጥረት ለመቅረፍ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር 20,000 ዩኒት ደም መሰብሰብ ታቅዷል፡፡

ሌላው የቤት ለቤት የሕክምና አገልግሎት መስጠት የበጋው የበጎ ፈቃድ ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ‹‹በጎነት በሆስፒታል›› መርሐ ግብር 550 በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለተግባራዊነቱ 11 የመንግሥት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች መመረጣቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

በወሰንና ድንበር የለሽ በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር 5,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ፣ የአርሶ አደሩን ሰብል የመሰብሰብ፣ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የመገንባት ሥራዎች በቀጣይ ወራት ይከናወናሉ፡፡

በአጠቃላይ በበጋ የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ላይ ከ246 ሺሕ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ፣ የኅብረተሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለማቃለል ጥረት እንደሚያደርግ፣ በዚህም ከ353 ሺሕ በላይ ወገኖች እንደሚጠቀሙ ይጠበቃል፡፡

በዚህም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ብቻ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ወጪን ማዳን እንደሚቻል ኮሚሽነሩ አስታውቋል፡፡

ባለፈው ክረምት ከአምስት ሺሕ በላይ ቤቶችን በማደስ፣ ከ28 ሺሕ በላይ ቤተሰቦች ተጠቃሚ መሆናቸውን፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በማዕድ ማጋራት፣ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በደም ልገሳ፣ በመንገድ ትራፊክ ማስተባበር፣ በመጻሕፍት ማሰባሰብና በሌሎችም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ብቻ አራት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብር ወጪ ማዳን መቻሉን ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...