በአስተናጋጇ ኳታር ላይ ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ የተሰነዘረውን ቅሬታ ተከትሎ የተናገሩት፡፡ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት መግለጫ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብትን ጨምሮ ‹‹ኳታር የሰብዓዊ መብቶችን አታከብርም›› የሚለውን የአውሮፓውያኑን ትችት ያጣጣሉት ወደ ራሳቸው እንዲመለከቱ በማሳሰብ ነው፡፡ አውሮፓዊ መሆናቸውን ያስታወሱት ኢንፋንቲኖ፣ ‹‹እኛ አውሮፓውያን ለሰዎች የግብረገብ ትምህርት ከመስጠታችን በፊት ለ3,000 ዓመታት በዓለም ላይ ስናደርግ ለነበረው ነገር ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል ሲሉ በአፅንዖት ተናግረዋል።