በዓረባዊ ምድር ለመጀመርያ ጊዜ በኳታር የተዘጋጀውና ለአንድ ወር የሚዘልቀው 22ኛው የ2022 የዓለም ዋንጫ፣ በአል ባይት ስታዲየም እሑድ ኅዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በልዩ ልዩ የጥበባት ትርዒት ተጀምሯል። ግማሽ ሰዓት በዘለቀው የመክፈቻ መሰናዶ አሜሪካዊው የፊልም በኩር ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን እና በዩቲዩብ በሚያቀርበው መሰናዶ የታወቀው የኳታር ልጅ ጋኒም አል ሙፍታህ በመድረኩ ጎልተው ታይተዋል፡፡ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የተደረሰው ‹‹ድሪመርስ›› የተሰኘው ዘፈንን ደቡብ ኮሪያዊው የፖፕ አቀንቃኝ ጆንግ ኩክና የኳታሩ ድምፃዊ ፉዓድ አል ኩባሲ እየተቀባበሉ ዘፍነዋል። ፎቶዎች የመክፈቻ ሥነ በዓሉን በከፊል ያሳያሉ፡፡
ፎቶ፡ ገልፍኒውስ