Thursday, September 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅዝንቅ

ዝንቅ

ቀን:

ስኮትላንዳዊው በጣም ተቸግሯል፡፡ የንግድ ሥራው ተሰነካክሎ ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ነበር፡፡ በቀቢፀ ተስፋ ተውጦ ፈጣሪውን፣ ‹‹እባክህን እርዳኝ፤ የመጠጥ ግሮሰሪዬ ተሸጠ። አሁንም ቶሎ ገንዘብ ካላገኘሁ ቤቴ በሃራጅ መሸጡ አይቀርም፡፡ ስለዚህ እባክህን ሎተሪ እንዲደርሰኝ እርዳኝ›› እያለ ተማፀነው። ሎተሪ በወጣበት ምሽት ግን ዕድሉ ለእሱ ሳይሆን ለሌሎች ሰዎች ደረሰ። ተስፋ ሳይቆርጥ ‹‹አምላኬ፣ እባክህን ዕርዳኝ፤ የመጠጥ ግሮሰሪዬን፣ ቤቴንና መኪናዬን ሁሉ አጥቻለሁ!›› ብሎ እያስቀሰ ለመነ፡፡ ሆኖም በቀጣዩ ጊዜም ሎተሪ አልደረሰውም፡፡

ነገር ግን አሁንም ልመናውን አላቋረጠም፡፡ ‹‹ግሮሰሪዬ፣ ቤቴ፣ መኪናዬ፣ የቤት ዕቃዎቼ በሙሉ ተሸጡ፡፡ አሁን ደግሞ ቤተሰቤ እየተራበ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እምብዛም አስቸግሬህ አላውቅም። ታዛዥህ እንደሆንኩም ታውቃለህ። እባክህን ሎተሪ እንዲደርሰኝና እንድቋቋም እርዳኝ!›› እያለ በመደጋገም ፈጣሪውን ተማፀነው፡፡ በመጨረሻ ኃይለኛና የሚያጥበረብር ብርሃን ታየ። እግዚአብሔር መንበሩ ላይ እንደተቀመጠ እያናገረው ነበር። ‹‹ሰውዬ፣ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳን መጥተህ ልትቀበለኝ በተገባ፡፡ እስኪ በመጀመርያ የሎተሪ ቲኬት ግዛ አለው።

አረፈዓይኔ ሐጎስ ‹‹የስኮትላንድ ቀልዶች››

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...