Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዳያስፖራ አካውንትን ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያዋሉ ግለሰቦች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

የዳያስፖራ አካውንትን ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያዋሉ ግለሰቦች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ቀን:

በፋይናንስ ወንጀል የተሰማሩ አካላት የሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ላይ ክትትል የሚያደርገው የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የዳያስፖራ አካውንትን ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያዋሉ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ መንግሥት የሚወስዳቸው የተለያዩ ዕርምጃዎች ውጤት እንዳስገኙት ሁሉ፣ ለሕገወጥ የፋይናንስ ወንጀሎች መበራከት በር መክፈቱን በርካታ የፋይናንስ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይደመጣል፡፡

በፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት የፋይናንስ ወንጀሎች ትንተና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮናስ ማሞ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የዳያስፖራ አካውንት ራሱን የቻለ ጥቅምና በርካታ ጥሩ ጎኖች ቢኖሩትም፣ ግለሰቦች ያንን ሕግ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እየተጠቀሙበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹የዳያስፖራ አካውንት ዕሳቤው ግለሰቦች በዶላር አካውንታቸው ውስጥ ገንዘብ ማስቀመጥ እንዲችሉ ነው፡፡ አሁን ግን እየተደረገ ያለው ግለሰቦች ውጭ አገር ባልሄዱበት ሁኔታ ከጥቁር ገበያ ዶላር በመግዛት ወደ ዶላር አካውንታቸው የሚያስገቡበት ሁኔታ በተቋማችን ተረጋግጦ ከፍተኛ የሆነ ሥራ እየሠራን እንገኛለን፤›› በማለት አቶ ዮናስ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ግለሰቦች በውጭ ምንዛሪ የሚያስገቡትንና ለራሳቸው አገልግሎት እንዲጠቀሙበት የተፈቀደውን አሠራር ወደ ጎን በመተው የውጭ ምንዛሪውን ለሌሎች አሳልፈው በመስጠት ያልተገባ ተግባር እየተፈጸመ መሆኑን በመረዳት የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ  መመርያዎችን ማሻሻሉ ይታወሳል፡፡

አብዛኛው ሕገወጥ ገንዘብ የሚንቀሳቀሰው ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም መሆኑን የሚስታውሱት ኃላፊው፣ የሚወጡ ሕጎች በራሱ ለዚህ ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ክፍተት እንዳለቸው ገልጸዋል፡፡

‹‹በሌላ በኩል ግለሰቦች ውጭ አገር ሄደው ሲመጡና በጉምሩክ ሲያፀድቁ፣ ይዘውት የመጡት አንድ ሺሕ ዶላር ከሆነ የዲክለራሲዮኑን ሙሉ ቁጥር በመጠቀምና ሰነዱን ተጠቅመው ሌላ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት 200 ሺሕ ዶላር ነው ይዘን የመጣነው በማለት ቀሪውን ከጥቁር ገበያ በመሰብሰብ ወደ ዶላር አካውንታቸው የሚያስገቡ በርካታ ግለሰቦች አሉ፤›› ያሉት አቶ ዮናስ፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ንረቱ ከመጨመሩ በፊት የሚመለከታቸው በራሳቸው ኃላፊነቶች ስለሚያኩሩ ጥምረቱ ብዙም የጠነከረ እንዳልነበር አስታውሰው፣ በዚህ ወቅት ግን በተለይ ብሔራዊ መረጃ ደኅንነት፣ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ባንክ እንዲሁም የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖረው በጥቁር ገበያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የምንዛሪ መዛባት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል  የወንጀሉ ተዋንያኑን በመከታተል የባንክ እንቅስቃሴያቸውን ማገድና በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላም ሆነ በዶላር ላይ ተሳትፈዋል የሚባሉ የአቋማሪ ድርጅቶች፣ አስመጪዎች፣ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች፣ ደላሎች ላይ ጭምር ዕርምጃ እያስወሰደ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋር እየሠራ መሆኑን አቶ ዮናስ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...