Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ ልማትን ለማጠናከር የተደረሰው ስምምነት

የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ ልማትን ለማጠናከር የተደረሰው ስምምነት

ቀን:

በአበበ ፍቅር

በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ልማት፣ በሥራ ዕድልና በኢንተርፕረነርሺፕ እንዲሁም በሥራ ላይ ደኅንነትና ጤንነት ላይ የጋራ ዕቅድ አውጥተው ለመተግበር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱ ኅዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲደረግ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ስምምነቱ የጥራት መሠረታዊ ደረጃዎችን ከሚያወጣውና ከሚመራው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር አብሮ መሥራቱ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚከናወኑ ሥራዎችን ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል የንግድ ሥርዓቱን ለማዘመን የተጀመሩትን ተግባራት ዕውን በማድረግ ሒደትም የክህሎት ልማቱና የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ላይ የሚሠሩ ሥራዎች  እንደሚኖሩም አክለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገበያ መር ሥልጠና የሚከተል በመሆኑ፣ ምን ይፈልጋል የሚለውን ከማወቅ ጀምሮ በውስጡ ያሉ ፍላጎቶችን ከማሟላትና ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ያለውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

ምርቶቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ ሒደት የጥራት መሠረተ ልማቶች ደረጃን በተመለከተ የሚሠራና የሚያስተባብር ተቋም እንደመሆኑ በጋራ የሚሠሩ ተግባራት አሉ ብለዋል።

የተለያዩ ኢንተርፕራዞችን በመደገፍና በመከታተል በኩል ሚኒስቴሮቹ ጥራትን መሠረት ያደረጉና ተወዳዳሪ ምርቶችን በማምረት ረገድ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል። የክህሎት ልማት ሥራውንም ጎን ለጎን በማስኬድ ምርቶች የጥራት ደረጃቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል ተቋሙ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ሚንስትሯ አብራርተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ ለንግዱ ማኅበረሰብ  ተወዳዳሪነትና ቅልጥፍና ወሳኝ የሆነውን የሰው ኃይል ምርታማነት ለማሻሻል፣ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ክህሎትን ማሳደግ የሚገባ በመሆኑ፣ የጋራ ሥራን ለመሥራት ከሚኒስቴሩ ጋር ስምምነት መዳረሱን ተናግረዋል።

ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚጠበቅ በመሆኑ በተለይም ወጣት ምሩቃን አዳዲስ ሥልጠናዎችን ወስደው በፈለጉት የሥራ መስክ እንዲሰማሩ፣ ከክህሎት ሥልጠና በተለይም ከኢንተርፕረነርሽፕና ከሙያ ሥልጠና በኋላ ሥራ በማስጀመር ረገድ ሚኒስቴሩ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል። ወደ ሥራም ከገቡ በኋላ ምርቶቻቸው በገበያ ላይ በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከጥራት መሠረተ ልማት ጋር የተያያዙ ግብዓቶችን እንደሚያመቻቹ ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...