Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየሩሲያ ጦርነት ማቆምን አጀንዳ ያደረገው የቡድን 20 ጉባዔ

የሩሲያ ጦርነት ማቆምን አጀንዳ ያደረገው የቡድን 20 ጉባዔ

ቀን:

በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት ዘጠኝ ወራትን አስቆጥሯል፡፡ ይህም የአገሮቹን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ኢኮኖሚ አንገዳግዷል፡፡ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር፣ የምግብ እጥረትና ውድነት እንዲከሰትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

አገሮቹ በገቡበት ጦርነት ምክንያት በተለይ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች ወድመዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ተሰደዋል፡፡ ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ በርካቶች ተገድለዋል፡፡

ጦርነቱ ያበቃና በዩክሬን ጎተራ ያጣበቡ ሰብሎች ለውጭ ገበያ ያቀረቡ ዘንድ ከዚህ ቀደም ስምምነት ተደርሶ ተስፋ ታይቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ እህል የሚተላለፍባቸው ኮሪደሮች ዳግም ተዘግተዋል፡፡

የዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት እልባት ባጣበት በአሁኑ ወቅት በኢንዶኔዥያ ባሌ ደሴት እየተካሄደ ባለውና ዛሬ በሚያበቃው የቡድን 20 አገሮች ጉባዔ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውም ይኸው የአገሮቹ ጦርነት ያስከተለው ቀውስና ሩሲያ ተጠያቂ መሆን አለባት የሚለው አጀንዳ ነው፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ዜሌኒስኪ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ያስተላለፉትን ንግግር ጠቅሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ጦርነቱ አሁን መቆም አለበት፡፡ የቡድን 20 አባል አገሮችም ዩክሬን የምታቀርበውን የሰላም ዕቅድ መደገፍ አለባቸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ እንደሚሉት፣ ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ታርተርንና ዓለም አቀፉ ሕግን መሠረት አድርጋ ጦርነቱን አሁኑኑ ልታቆም ይገባል፡፡

‹‹እያንዳንዱ ቀን ባለፈ ቁጥር አዳዲስ የዩክሬናውያን ሞት አለ፣ ለዓለም አዲስ ሥጋት ነው፣ ለሁሉም የዓለም ሕዝቦች ኪሣራ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የቡድን 20 አገሮች መሪዎች በኑክሌር ደኅንነት፣ የምግብና የኃይል አቅርቦት ደኅንነትና የዓለም አቀፍ ሕግ ወደ ቦታው እንዲመለስ ዕርምጃ እንዲወስዱም ጠይቀዋል፡፡

‹‹ሩሲያ የሰላም ቀመሩን የማትቀበል ከሆነ የምትፈልገው ጦርነት ብቻ ነው፤›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ የጨረር ልቀትና ሰብልን ወደ ውጪ የመላክ ደኅንነት ላይ ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ የሚመረምር ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፣ ዩክሬን ለገጠማት ውድመትም ካሳ እንዲከፈልም አሳስበዋል፡፡

ሮይተርስ እንደሚለው አሜሪካ የቡድን 20 አባል አገሮች ስብስባቸውን ዛሬ ኅዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያጠቃልሉ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነትና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የደረሰውን ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲያወግዙ ትጠብቃለች፡፡

ኅዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በነበረው ጉባዔ አብላጫው አጀንዳ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን፣ ከእነዚህ አንድም አሜሪካና አጋሮቿ የሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ትክክል አይደለም የሚለው ሪሶሊውሽን ላይ ሲሆን በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የተመራው የሩሲያ ልዑክ ሪሶሊውሽኑን አጣጥሎታል፡፡

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮንና የቻይናው ፕሬዚዳንት ቺ ጁፒንና ጦርነቱን በማቆምና የኑክሌር ጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ እንዳይውል መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ተመድ በበኩሉ ሩሲያ በዩክሬን ለደረሰችው ውድመት ካሳ እንድትከፍል ያቀረበውን ጥሪ ሩሲያ አጣጥላለች፡፡

ተመድ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስህተት የተባሉ ድርጊቶችን በዩክሬን በመፈጸሟ ለማንኛውም ጉዳትና ውድመት ካሳ ልትከፍል ይገባል የሚል ነው፡፡

የተመድ አባል አገሮችም ከዩክሬን ጋር በመተባበር ሩሲያ ፈጽማለች የሚባሉ ጉዳቶችን በማስረጃ እንዲያጠናክሩ ምክረ ሐሳብም አቅርቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ የውሳኔ ሐሳቡን የተቀበሉት ቢሆንም፣ የውሳኔ ሐሳቡ የሚፀድቀው አባል አገሮች ሲስማሙበት ው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...