Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበማኅበር ቤት ለመሥራት ለተመዘገቡ ቆጣቢዎች በቅርቡ ዕጣ  እንደሚወጣ ተገለጸ

በማኅበር ቤት ለመሥራት ለተመዘገቡ ቆጣቢዎች በቅርቡ ዕጣ  እንደሚወጣ ተገለጸ

ቀን:

  • ተጭበርብሯል ተብሎ ተሰርዞ የነበረው የ25,791 ቤቶች ዕጣ በድጋሚ ወጥቷል

ለጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) በ2005 ዓ.ም. የ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ተመዝግበው ከነበሩት ውስጥ 4,500 ተመዝጋቢዎችን በማኅበር በማደራጀት በቅርቡ ዕጣ እንደሚያወጣ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

 ቢሮው በዚህ አማራጭ የሚገነቡ ቤቶችን ዲዛይን፣ የመሬት ዝግጅት፣ የፋይናንስ ምንጭ አበዳሪ ባንኮችን በማነጋገርና መሰል ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ ማኅበራቱን ለማደራጀት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቢቆይም፣ የ14ኛው ዙር ዕጣ አወጣጥ ይፋ እስኪደረግ መጠበቅ ግድ ሆኖበት መቆየቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሪት ያስሚን ወሃቢረቢ እንዳስታወቁት፣ ተሰርዞ በነበረው የ14ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ምክንያት የማኅበር ቤት ዕጣ ሳይወጣ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት ዕጣ መውጣቱን ተከትሎ በቀጥታ በማኅበር የማደራጀት ሒደት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ለ4,500 ቆጣቢዎች የማኅበር ቤት የማደራጀት የዝግጅት ምዕራፋችንን አጠናቀናል፤›› ያሉት ወ/ሪት ያስሚን፣ ለዚህም የሚሆን መሬት እንደተለየና ከባንክ ጋር ያሉ ውይይቶችም በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ማኅበራቱ ከተደራጁ በኋላ በቀጥታ ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚደረግ መሆኑን፣ ከዚህም በኋላ በቤት ልማት አማራጩ የመገንባት ሒደትን የማስፋት ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡

‹‹ለከተማው ነዋሪ የቤት ችግርን መቅረፍ እንደፈለግነው አልሄደልንም፣ ብዙ ውስብስብ ነገሮች ስላሉት፣ ግን ደግሞ መተው የሚቻል ጉዳይ አይደለም፤›› ያሉት ኃላፊዋ፣ በትናንትናው ዕለት ለዕድለኞች የተላለፉትን 25,791 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ቀሪ ከመሠረተ ልማት ጋር ተያይዞ ያልተጠናቀቁትን ሥራዎች በማከናወን እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስረድተዋል፡፡

ወ/ሪት ያስሚን እንደተናገሩት፣ የቤት ልማትን በግሉ ዘርፍ በስፋት ማስኬድ እንደ አማራጭ ታይቶ ለዚያ የሚሆን የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ ደንቡ በምክር ቤት ጭምር ፀድቆ ወደ ሥራ መግባቱን፣ ለዚህም የመንግሥትና የግል አጋርነት ቦርድ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡ ቦርዱ የቤት ልማት ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ፕሮጀክቶች እንደሚመራ፣ ነገር ግን የቤት ልማት ዘርፍ ቅድሚያ የተሰጠው ተግባር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከውጭ የቤት አልሚ ኩባንያዎች ጋር የተደረጉ ንግግሮችና የአዋጭነት ጥናት ሥራ የተመለከቱ እንቅስቃሴዎችን ያስታወሱት ኃላፊዋ፣ ነገር ግን በዚህ ወቅት ካለው የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ ጋር ተያይዞ በውጭ ኩባንያዎች የሚቀርበው የካሬ ዋጋ ከፍ ስላለ በዚያ ላይ ውይይቶችና ድርድሮች እየተደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት በ20/80 እና 40/60 የቤቶች ልማት ፕሮግራም፣ በመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ እንዲሁም በባለሀብቶችና የግል አልሚዎች 61,509 ቤቶች ለመገንባት እንደታቀደ ከዚህ ቀደም ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፣ በትናንቱ የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት 100 ሺሕ የሚደርሱ ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር፣ እንዲሁም የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች ዕጣ ኅዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ሥነ ሥርዓት አውጥቷል፡፡ ቤቶቹ በበርካታ ችግሮች ማለትም የፋይናንስ እጥረት፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦት፣ የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መናርና እጥረቶች፣ የተቋራጭ መጥፋትና ሌሎችም ችግሮች የተወሳሰቡ ችግሮችን እንዳለፉና ችግሮቹን ለመፍታት አስተዳደሩ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንክ በብድር መውሰዱን አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...