Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጤናና ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለሀብት በአሜሪካ ኮንግረስ ተሸለሙ

በጤናና ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለሀብት በአሜሪካ ኮንግረስ ተሸለሙ

ቀን:

ኑሮአቸውን በውጭ አገር ካደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በጤና፣ በትምህርትና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉት ባለሀብት አቶ ስማቸው ከበደ ከአሜሪካ ኮንግረስ የምስጋናና ዕውቅና ሰርተፊኬት ተሸለሙ፡፡

መሠረቱን አሜሪካ ያደረገው ፒፕል ቱ ፒፕል የተባለው ድርጅት 14ኛ ዓመታዊ ስብሰባውን ኦክቶበር 15 ቀን 2022 በዋሽንግተን ዲሲ ባካሄደበት ዕለት የምሥጋናና ዕውቅና ሰርተፊኬት የተሸለሙት ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉ ሌሎች ትውልደ ኢትዮጵያውያንም እንደነበሩ ታውቋል፡፡

ድርጅቱ በየዓመቱ በተለያዩ የሕክምና ሙያና በተለያዩ የዕውቀት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክ የሚናገሩት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር እናውጋው መሐሪ (ዶ/ር)፣ ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ የሕክምና ቦታዎች በመዘዋወር በተለያዩ ሕመሞች ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን የነፃ ሕክምና እንደሚሰጡ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሕክምና ባለሙያዎቹ በነፃ ለሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የሆቴል አገልግሎት በመስጠትና በማስተባበር ከ14 ዓመታት በላይ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኙት የቀድሞ ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴልና በአሁኑ ኢንተር ሌግዢሪ ሆቴል ባለቤት የሆኑ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ተመሳሳይ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሌሎች ባለሀብቶችና በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሙያዎች ጋር ተወዳድረው አሸናፊ በመሆናቸው የአሜሪካ ኮንግረስ የምሥጋናና የዕውቅና ሰርተፊኬት እንደሸለማቸው እናውጋው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በውጭ አገሮች የሚሠሩ በርካታ የሕክምና ባለሙያዎች በዓመት አንድ ጊዜ በፈቃደኝነት ነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ጠቁመው፣ ከሕክምና በተጨማሪ በትምህርት፣ በተለያዩ ልማቶችና ሌሎች በጎ ተግባራትንም እንደሚፈጽሙ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የደም፣ የኩላሊት፣ የልብ፣ የአዕምሮ፣ የሳንባና ሌሎችም በርካታ ሕክምናዎች መሰጠታቸውንና እየተሰጡ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከባህር ዳር፣ ከወሎ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሰመራ፣ ሐዋሳ፣ ቦንጋ፣ አርሲና ሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር እየሠራ ለሚገኘው ፒፕል ቱ ፒፕል፣ አቶ ስማቸው በገንዘብና በተለያዩ ሁኔታዎች እገዛ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን እናውጋው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ይህ በጎ ተግባራቸውም ለአሜሪካ ኮንግረስ ቀርቦና ተወዳዳሪዎቹን በማሸነፍ ሊያሸልማቸው እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

ፒፕል ቱ ፒፕል በጦርነት የፈረሱ በአማራና በአፋር ክልሎች የሚገኙ አሥር ትምህርት ቤቶችን ማስጠገኑንና ማሠራቱን፣ እንዲሁም አሁን ሰላም ከወረደ ትግራይን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎችም ይህንን ተግባሩን እንደሚቀጥል እናውጋው (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...