Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓባይ ባንክ ለተቋራጭ ኩባንያ የገባውን 306 ሚሊዮን ብር ዋስትና እንዲከፍል ተፈረደበት

ዓባይ ባንክ ለተቋራጭ ኩባንያ የገባውን 306 ሚሊዮን ብር ዋስትና እንዲከፍል ተፈረደበት

ቀን:

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለተክለ ብርሃን አምባዬ ተቋራጭ ገብቶለት የነበረውን አጠቃላይ ዋጋቸው 305.9 ሚሊዮን ብር የሆኑ ሁለት የቅድመ ክፍያ ዋስትናዎች፣ ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እንዲከፈል አዘዘ፡፡ አስተዳደሩ የተፈረደለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከወሰደው ከአንድ ዓመት በላይ ከተከራከረ በኋላ ነው፡፡ ውሳኔ የተሰጠው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ኮንስትራክሽን ችሎት ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ባንኩ ገንዘቡን ከመስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሚቆጠር ዘጠኝ በመቶ ወለድ ጭምር እንዲከፍል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አስተዳደሩና የተክለ ብርሃን አምባዬ ተቋራጭ ነሐሴ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በገቡት የመጀመርያ ውል መሠረት፣ በኦሮሚያ ክልል ከአቦምሳ – አስኮ – ዲቡ ወንዝ 60.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ በ1,095 ቀናት እንዲጠናቀቅ ነበር፡፡ ለዚህም 991.7 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ የፕሮጀክት ውል የገቡ ሲሆን፣ ሥራውን ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ለማስጀመርና ለቅድመ ክፍያ የሚሆን 20 በመቶ ወይም 176.8 ሚሊዮን ብር እንዲፈጽም ተስማምተው ክፍያው የተፈጸመ ሲሆን፣ ባንኩም ለዚህ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ዋስትና ገብቶ መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ማረጋገጫ መስጠቱን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ይገልጻል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በገቡት ሁለተኛው ውል ደግሞ፣ ከዲቡ ወንዝ-  በደዩ-ጨለለቃ የሚሄደውን የ44.42 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ በ725.6 ሚሊዮን ብር እንዲሠራ፣ ነሐሴ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ተፈራርመዋል፡፡ ይህ ውልም ሥራውን በ1,095 ቀናት እንዲጠናቀቅ ተፈራርሞ የነበረ ሲሆን፣ ሥራው ከጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲጀመርና ለሥራውም ማስጀመርያ 20 በመቶ ወይም 129.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ እንዲከፍል ተስማምተው ነበር፡፡ ለዚህም ክፍያ ዓባይ ባንክ መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአስተዳደሩ ቅድመ ክፍያ ዋስትና መግባቱን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ላይ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፍርድ ትዕዛዙ እንደሚገልጸው፣ አስተዳደሩ ለተቋራጩ ባሳየው የፕሮጀክት መጓተትና ቸልተኝነት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኋላ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ሁለቱንም ውሎች አቋርጧል፡፡

ውሎቹ በተቋራጩ ጊዜ ለመጀመርያው ውል በአምስት ወራት መካሄድ የነበረባቸው ቅድመ ማስኬጃ ሥራዎች በ23 ወራት አለመካሄዳቸውና ውሉን ባቋረጠ ጊዜም መጠናቀቅ ሲገባው ገና 19.3 በመቶ ላይ ብቻ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ በተመሳሳይ በሁለተኛው ውል መሠረት በ120 ቀናት መጠናቀቅ የነበረባቸው የቢሮ ግንባታዎች፣ ላቦራቶሪዎችና መኖሪያ ቤቶች አለመጠናቀቃቸው፣ እንዲሁም ውሉ ሲቋረጥ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ይዘት 32.84 በመቶ ብቻ የተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህንንም የቅድመ ክፍያ ዋስትና ለማስመለስ ሲሆን አስተዳደሩ መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም. የመጀመርያውን ውል ወደ ክስ የወሰደው ሲሆን፣ ለሁለተኛው ውል ደግሞ ቀደም ብሎ ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር፡፡

ባንኩ የተለያዩ መከራከሪያዎችን በማምጣት መክፈል እንደሌለበት ቢከራከርም በፍርድ ቤት ተቀባይት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...