Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ቀን:

ዝምታም መልስ ነው

ኡመር ካይም መንገድ ላይ እየሄደ አንድ ሰው በአደባባይ ‹‹ሰካራም ፣ ሃይማኖት የለሽ፣ አጭበርበሪ፣ ሌባ!›› እያለ የስድብ ዓይነት ያወርድበት ጀመር። እንደዚህ እየተሰደበ ኡመር ካይም ግን ይስቅ ነበር።

 አንድ ሽክ ብሎ የለበሰና ስድቡን ይሰማ የነበረ ሰው ‹‹እንዴት አንድም መልስ ሳትስጥ ይን ሁሉ ስድብ ዝም ብለህ ትሰማለህ? አይሰማህም?›› በማለት ኡመር ካይምን ጠየቀው። ኡመር ካይም ምንም መልስ ሳይሰጥ ሰውየውን ተከትለኝ በማለት እየመራ ወደ አንድ መጋዘን ይዞት ገባና በጣም የቆሸሸ ቡትቶ ልብስ አንስቶ ወደ ስውየው እየወረወረ ‹‹እስኪ ከላይህ ላይ ደርበው። ከለበስኸው ልብስ ጋር አብሮ ይሄዳል?›› አለው
ሽክ ብሎ የለበሰው ሰውዬም የወረወረለትን ቡትቶ አገለብጦ እያየ ‹‹ምንድን ነው ይህ ቆሻሻ ዘባተሎ? በዚህ በለበስሁት ልብስ ላይ እንዴት ይህን ደርብ ትለኛለህ? ዕብድ ነህ?›› በማለት ቡትቶ ጨርቁን መልሶ ወረወረው።

‹‹አየህ›› አለ ኡመር ካይም ‹‹አንተ ቆሻሻውን ልብስ መሞከር አልፈለግህም። በተመሳሳይ እኔም ያ ሰው ይወረውራቸው የነበሩ አፀያፊ ቃላትን መሞከር አልፈለግሁም፡፡ በዚህ ዓይነት ሰው ስድብ ስሜታዊ መሆንና እሱ የተጠቀመበትን ቃላት መጠቀም ማለት ሌላ ሰው የወረወረውን ቆሻሻ ቡትቶ ልብስ እላይህ ላይ እንደ መደረብ ይቆጠራል›› በማለት ለምን ትዕግሥትን እንደመረጠ ለሰውየው አስረዳው።

– አማረ ገሠሠ ‹‹ዊዝደም›› (2007)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...