ስኮትላንዳውያን አምፖሎቻቸው ሲቃጠሉባቸው ምን ያደርጋሉ? ባስቸኳይ ተሰባስበው የራስ አገዝ ቡድን ያቋቁማሉ፤ ጨለማን ተቋቁሞ የመኖር ዘዴ የተሰኘ ማኅበር።
ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ ኮሚቴ ያቋቁሙና አንዱ አምፖሉን መለወጥ እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ ደብዳቤ ይጽፋል። ሁለተኛው በጀት ይመድባል። ሦስተኛው አምፖሉን ያወርዳል፡፡ አራተኛው አምፖል እንዲገዛ ትዕዛዝ ያስተላልፋል። በመጨረሻም አምስተኛው አምፖሉ ሊተካ እንደሚገባ ለጸሐፌ ትዕዛዙ ያስተላልፋል።
ቱሪስት፡- ‹‹የተቃጠለ አምፖል ለመተካት ስንት ስኮትላንዳውያን ያስፈልጋሉ?››
ስኮትላንዳዊ፡- ‹‹ኧረ ገና መቼ ጨለመና!››
የተቃጠለ አምፖል ለመቀየር ስንት ስኮትላንዳውያን ያስፈልጋሉ? ስኮትላዳዊያን አምፖል አይቀይሩም፤ ጨለማ ውስጥ መቀመጥ ስለሚረክስ ያን ይመርጣሉ።
- አረፈዓይኔ ሐጎስ ‹‹የስኮትላንዳዊያን ቀልዶች››