Thursday, September 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሙቀትን የሚፈጥሩት እነማን ናቸው?

ሙቀትን የሚፈጥሩት እነማን ናቸው?

ቀን:

ቀደም ብሎ በውጪ አገር የፊዚክስ ድኅረ ምረቃ ተማሪ የነበረና በአዕምሮ መታወክ የተነሳ ትምህርቱን ያቋረጠ፣ አንድ ገላጭ ንድፈ ሐሳብ ይዞ ቀረበ።  ይኸውም እንዲህ የሚል ነው፣ ‹‹ሙቀትን የሚፈጥሩት ‘የማክስዌል ዲመንስ’ ወይም አጋንንት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ቅዝቃዜ የተከሰተው አጋንንቱ ተፈላጊውን የእርግብግቦሽ መጠን መስጠት ባለመቻላቸው ነው። ይህም የሆነው በአጋንንቱ ኢነርጂ ማጣት፣ የተመጣጠነ ምግብ አለማግኘት ነው። በዚህም የተነሳ ለአጋንንት የሚከተለውን ጥሪ አቅርበናል›› ይላል ወጣቱ፣ ‹‹አጋንንት ሆይ! ባላችሁበት፣ በአየሩ፣ በባህሩ፣ በምድሩ፣ መልዕክቴ ይድረሳችሁ። ይህን መፈክር አንግባችሁ ተነሱ፣ ‹‹ጭቆና ይብቃ! ብጣሽ ጥብሳ ጥብስ ይወረወርልናል፣ ምግባችን አምድና አተላ ነው! ይህ መቆም አለበት፣ እኛም ዕድል ይድረሰንና ከማዕዱ እንቅረብ! እስከ  መቼ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንታያለን? እኛም እኮ እንራባለን፣ እንጠማለን፣ እንታረዛለን፣ እኛ አስታዋሽ ያጣን ሕዝቦች ነን፣ እስቲ ተመልከቱት፣ የሰው ልጆች ትምህርት ቤት ገብተው ፊደል ይቆጥራሉ፣ የእኛ ልጆች ሙያ ተምረው አገራቸውንና እራሳቸውን ለመደገፍ ይጥራሉ፣ የኛዎቹ ሙያቸው ክፋት፣ ችግር፣ ጥፋት ነው። ይህ ሁኔታ እንደዚህ ከቀጠለ የዘለአለም ፀፀት ሊከሰት ይችላል! ነፃነት፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነት! የዓለም ጭቁን አጋንንት ተባበሩ! እናሸንፋለን!››

– ግርማ ሙልኢሣ  ‹‹ለጭውውት ያህል›› (ክብሩ ቡክስ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...