የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳስታወቁት፣ በቆቦ፣ ሮቢት፣ ዞብል፣ ጎቢዬና ዋጃ የመልሶ ጥገና ተከናውኖ የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረ ሲሆን፣ እንዲሁም በዛሬው ዕለት አድርቃይ ላይ አገልግሎቱ መጀመሩን አስታውቀዋል።
በአላማጣና ኮረም አካባቢዎች እንዲሁ የቴሌኮም አገልግሎቱ በአጠረ ሰአት ይጀምራል ተብሏል ።
ኩባንያው የጥገና ባለሙያዎችን አሰማርቶ የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመረ ሁለት ሳምንታት እንዳስቆጠረ ያስታወቀ ሲሆን፣ በቀሪ አካባቢዎች የሚደረገው ጥገና እግር በእግር የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።