Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

[ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ ምርት የተገኘው ውጤት የሕዝባችንን የምግብ ፍላጎት የሚመልስ ብቻ ሳይሆን ለአገር ክብርና ኩራት የፈጠረ መሆኑን ሲገልጹ አማካሪያቸው ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰማውን ትችት እያካፈላቸው ነው] 

ቀን:

  • የስንዴ ምርት ልማቱ ጥሩ ቢሆንም አንዳንዶች ትችት እያቀረቡበት ነው።
  • ምን ብለው ተቹ
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ጤፍ እንጂ ስንዴ አዘውትሮ አይመገብም እያሉ ነው።
  • ድርቅና ረሃብ ሲገጥመን ግን የሚያቀርቡልን ዕርዳታ ስንዴ ነው። አይደለም እንዴ?
  • ልክ ነው። ግን እነሱ ምክንያታዊነት አያስጨንቃቸውም።
  • እንዴት?
  • በቃ መቃወም ከፈለጉ መቃወም ነው። ለዚያውም እስከ ጥግ ድረስ ሔደው የማይገናኝ አገናኝተው ነው የሚቃወሙት።
  • ለምሳሌ?
  • ሌላ ምሳሌ አያስፈልገንም። በዚሁ የሰንዴ ልማት ላይ ምን እያሉ መሰለዎት?
  • እ …
  • ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስበው አይደለም።
  • እና ለማን ነው?
  • ለራሳቸው ነው።
  • ለእኛ ምን ያደርግልናል?
  • ሥልላጣናቸውን ለማራዘም።
  • ኦ..ኦ.. እዚህ ድረስ ዝቅ ብለዋል?
  • ለእኔም ግራ ገብቶኛል።
  • ምኑ ነው ግራ ያጋባህ?
  • ለምን በዚህ ደረጃ ለመቃወም እንደፈለጉ ለመረዳት ተቸግሬያለሁ። አንዳንዶቹ እኮ የሚናገሩት ግራ ያጋባል ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን ይላሉ?
  • በዚህ መጠን የሰንዴ ልማት ውስጥ መግባት ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ሳይረዱ ቀርተው አይደለም። አውቀው ነው እያሉ ነው።
  • ምን ተፅዕኖ ያመጣል ነው የሚሉት?
  • ሌሎች አዝዕርቶች በኢትዮጵያ እንዳይመረቱ ያደርጋል እያሉ ነው።
  • ምን?
  • አዎ። ሌሎች አዝዕርቶችን ለማጥፋት ነው እስከማለት ደርሰዋል።
  • ይደንቃል። ስንዴ ላይ ይህን ያክል ተቃውሞ?
  • በዚህ ጭፍን ተቃውሞ ከቀጠሉ በቅርቡ አንድ ነገር ማለታቸው አይቀርም፡፡
  • ምን ሊሉ ይችላሉ?
  • ጄኖሳይዳል ነው።
  • ምኑ?
  • የሰንዴ ልማቱ!

[ክቡር ሚኒስትሩ የሰሜኑን ግጭት ለመፍታት የተጀመረውን ድርድር በተመለከተ ከአማካሪያቸው ጋር ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  • የአንድ ድርድር ውጤታማነት በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሁኔታ ወይም ውጤት ይለካል ብሎ ማሰብ ትክክል ይመስልሃል?
  • እሱን እረዳለሁ ክቡር ሚንስትር። በእኛ ሁኔታ ግን ከሁለት አንዱ መስመር መያዝ ነበረበት።
  • ከሁለት አንዱ ማለት?
  • ወይ ድርድሩ ወይም ደግሞ በግንባር ያለው ሁኔታ መስመር መያዝ ነበረበት ማለቴ ነው።
  • ስንዴ እየዘራን መሰለህ እንዴ?
  • ኧረ ስለ ስንዴ አላወራሁም?
  • ታዲያ ምንድን ነው መስመር መስመር …መስመር መያዝ አለበት የምትለው?
  • ክቡር ሚኒስትር እኔ ብቻ ሳልሆን ማኅበረሰቡ ጭምር ቅር ብሎታል።
  • ለምን?
  • አለቃ ሰሞኑን ለውጭ ሚዲያ ስለድርድሩ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።
  • አላየሁትም። ምን አሉ?
  • አንደኛው ነጥብ የውጭ ጣልቃ ገብነት በዝቷል የሚል ነው።
  • እሺ …
  • የውጭ ጫና ከበዛ ሰላም ሩቅ ይሆናል በማለት ጫና መኖሩን ጠቁመዋል።
  • እውነት ነው። የውጭ ጣልቃ ገብነትና ጫናው ከፍተኛ ነው።
  • ክቡር ሚኒስትር ይህንንማ ራሳችን የፈቀድነው በመሆኑ ጫና እንደሚመጣ ወይም ጫናውን እንደምናመክነው መጀመሪያውኑ ማወቅ ነበረብን።
  • እንዴት?
  • የአፍሪካ ኅብረትም ይሁን ሌላ እንዲያደራድሩን የተስማማነው በፈቃዳችን አይደለም እንዴ?
  • እሱማ ነው!
  • ታዲያ አሁን ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትና ጫና ብለን መቃወም ተገቢ ነው?
  • ነገሩ አልገባህም። ምን መሰለህ?
  • እ …
  • አደራዳሪዎቹ አይደለም ጣልቃ እየገቡ ያሉት።
  • ማነው?
  • ታዛቢዎቹ ናቸው። ድርድሩም የተራዘመው በእነሱ ሴራ ነው፡፡
  • እንዴት?
  • መንግሥት ቡድኑ ትጥቅ መፍታት አለበት በሚለው አቋሙ ፅኑ ነበር።
  • እሺ …?
  • ቡድኑ ደግሞ በተቃራኒው ትጥቅ እንደማይፈታ ሽንጡን ገትሮ ሲሟገት የድርድሩ ማብቂያ ደረሰ።
  • እሺ …?
  • በኋላ ከታዛቢዎቹ ጋር ተመካክሮና ማስተማመኛ አግኝቶ አንድ ጉዳይ ይዞ መጣ።
  • ምን ይዞ መጣ?
  • ትጥቅ ለመፍታት እስማማለሁ አለ።
  • መጨረሻ ላይ?
  • አዎ።
  • እሺ የእኛ ተደራዳሪዎች ምን አሉ?
  • የእኛ ተደራዳሪዎች ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ታዛቢዎቹ በጉዳዩ በጥልቀት ለመነጋገር የድርድሩ ጊዜ መራዘም አለበት አሉ።
  • እሺ ከዚያስ?
  • ነገሩ የአቋም ለውጥ በመሆኑ የድርድር ጊዜው ተራዝሞ ውይይት ይደረግ ተባለ።
  • እሺ?
  • ወደ ዝርዝሩ ሲገባ ግን አዲስ ነገር የለም።
  • እንዴት?
  • ቡድኑ ትጥቅ ለመፍታት እስማማለሁ ነገር ግን ይህንን ተግባር የምፈጽመው በድርድሩ መጨረሻ ላይ ነው አለ።
  • ምን …?
  • አዎ። ትጥቅ ለመፍታት ዝግጁ ነኝ ግን ትጥቅ መፍታት አንዴ የሚተገበር ነገር አይደለም ስለዚህ ጊዜ ተወስዶ መፈጸም አለበት። እስከዛ ግን በሌሎች ጉዳዮች ድርድሩ ይቀጥል አለ።

ጊዜ መግዣ መሆኑ ነው?

  • እንደዚያ ነው። ግን የቡድኑ አይደለም የሚገርመው።
  • እ …?
  • የታዛቢዎቹ ነው።
  • ለምን?
  • ቡድኑ ትጥቅ ለመፈታት መስማማቱ አንድ ትልቅ ዕርምጃ በመሆኑ በእናንተ በኩልም አንድ ዕርምጃ መምጣት አለባችሁ አሉ።
  • ምን ጠየቁ?
  • ተኩስ ማቆም አለባችሁ!
  • ወደፊት ትጥቅ እፈታለሁ ስላለ?
  • አዎ። ለዚያ ነው አለቃ የውጭ ጣልቃ ገብነትና ጫና በዝቷል ያሉት፡፡
  • አሁን ግልጽ ሆኖልኛል ቢሆንም ግን …
  • ግን ምን?
  • አለቃ የተናገሩት ጫና ስለመብዛቱ ብቻ አይደለም።
  • ሌላ ምን ብለዋል?
  • ችግራችንን እኛው መፍታት እንችላለን ብለዋል።
  • እንደዚያ ያሉት ጣልቃ ለሚገቡት የውጭ ኃይሎች ነው።
  • እኔ ግን እንደዚያ ለማለት የፈለጉ አልመሰለኝም።
  • ምን ለማለት የፈለጉ ነው የመሰለህ?
  • እኛው እንታረቅ ያሉ አስመስለው ሌላ ነገር ለማለት የፈለጉ ነው የመሰለኝ።
  • ምን?
  • ገላጋይ አይግባ!

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...