Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርት ተጠቅመው የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርት ተጠቅመው የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

ቀን:

  • 2 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተዳርሰዋል

የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርትን ሙሉ ለሙሉ በመጠቀም የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡  

ባለሥልጣኑ ይህንን የገለጸው ማክሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በአፍ መፍቻ ቋንቋና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ያሉ ችግሮችንና መፍትሔዎችን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ፣ ከመንግሥትና ከግል ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ትተው የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርትን ተጠቅመው የሚያስተምሩ 26 የግል ትምህርት ቤቶች የመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም. የተጀመረው የሥርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተቋማት የመማር ማስተማር ሒደቱ ላይ ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማወቅ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለመጀመርያ ዙር ፍተሻ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ፍተሻው ለሁለተኛ ጊዜ ተግባራዊ መደረጉን፣ በፍተሻው ወቅትም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርትን ተጠቅመው እያስተማሩ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል ብለዋል፡፡

መንግሥት ያስቀመጠውን ሥርዓተ ትምህርት ወደ ጎን በመተው ከህንድ፣ ከእንግሊዝና ከሌሎች አገሮች ቀጥታ ገልብጠው የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶችን ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በማወያየት ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ መንግሥት ያስቀመጠውን ሥርዓተ ትምህርት የሚጥሱት የግል ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን፣ ችግሩን ለመቅረፍ 520 የሚሆኑ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ያካተቱ መጻሕፍትን ለግልም ሆነ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን 1.2 ሚሊዩን መጻሕፍትን ለተለያዩ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ተደራሽ መደረጉን፣ በዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተደራሽ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው የተደረገ መሆኑን፣ ነገር ግን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሶፍት ኮፒው አልደረሰንም የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...