በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በተጠራው 77ኛው የተመድ ስብሰባ ላይ የተናገሩት፡፡ በጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. የተመድ ውሎ ላይ ‹‹እየሰማን ያለነው የሰላም መልዕክት ሳይሆን ተከታታይ ማስጠንቀቂያዎችን ነው›› ያሉት አምባሳደሩ፣ ነገር ግን በርካታ የፖለቲካ ምስቅልቅሎችን ማለፍ እንደቻለች ኩሩ አፍሪካዊት፣ በርካታ ችግሮቻችንን ተጋፍጠን እንዳለፍናቸው ሁሉ፣ ዛሬም የገጠሙንን ችግሮች በእርግጠኝነት እንሻገራቸዋለን ብለዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተሳተፉት ተጠያቂ እንደሚደረጉ አስረግጠው የተናገሩት አምባሳደሩ፣ ዘላቂ ሰላም መስፈን የሚችለው በሁሉም አካባቢዎች ለተሠሩ ወንጀሎች ተጠያቂነትና ፍትሕ ሲሰፍን ብቻ መሆኑን፣ ይህም በአገሪቱ ባለቤትነት መመራት እንዳለበት። አስምረውበታል፡፡