Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሥራ ዕድሎችን የማመቻቸት ውጥን

የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸት ውጥን

ቀን:

በኢትዮጵያ የሚፈጠረው የሥራ ዕድልና የሥራ ፈላጊው ቁጥር የተጣጣመ አይደለም፡፡ በመሆኑም የአገሪቱ የሥራ አጥነት ምጣኔ ከፍ እያለ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እስከ 2030 ድረስ ለ20 ሚሊዮን ዜጎች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች በመመቻቸት ላይ መሆናቸውን የሥራ ዕድልና ክህሎት ሚኒስቴር ይገልጻል፡፡

‹‹አሶሴሸን ለታለንትድ ዴቨሎፕመንት በኢትዮጵያ›› ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ሲደረግ የተገኙት የሥራ ዕድልና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን እንዳብራሩት፣ በመመቻቸት ላይ ያሉትን ሁኔታዎች ለማሳካት በየዓመቱ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ይዘጋጃል፡፡

የሥራ አጥነት ችግሮች የሚታዩባቸው ከገጠር ይልቅ በከተሞች፣ ከሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ይልቅ በወጣቶች፣ ከወጣቶች ደግሞ በሴቶች ላይ መሆኑን፣ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆነው ሕዝብ በትምህርት ቤቶች የሚገኙ ወጣቶች በመሆናቸው የክህሎት ልማትን ማሳደግና ወጣቱን በሥራ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

‹‹መንግሥት የሥራ ዕድልን በማስፋት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ልዩ ልዩ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ነው፤›› ያሉት አቶ ንጉሡ፣ ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ወጣቶች በተለይ ሴቶች ከቅጥርና ከጠባቂነት ይልቅ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር እንዲችሉ፣ ባለሙያም ሆነው ኢንተርፕራይዝ መሥርተው፣ ተደራጅተውና ራሳቸውን ችለው ለሌሎችም የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማድረግ የተለያዩ የፋይናንስ፣ መሠረተ ልማት፣ የመሥሪያና የመሸጫ ቦታዎች አቅርቦት እንዲሁም የገበያ ትስስርና መንግሥታዊ ድጋፍችን የማድረግ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ያላት አገር በመሆኗ፣ ያለውን አቅም አውጥቶ ጥቅም ላይ ማዋል የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአሶሴሽን ፎር ታለንትድ ዴቨሎፕመንት ኢን ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ ገመቹ ዋቅቶላ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

 የሰው ኃይልን ማልማት በሁሉም ዘርፍ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የታለንት ልማት ለመንግሥት ወይም ለተወሰኑ ድርጅቶች ብቻ ሳይተው፣ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ተሳትፎ ተደርጎበት ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አክለዋል፡፡

ዘላቂ የታለንት ልማት ሥነ ምኅዳር የሚገነባውም ሁሉም የድርሻውን ሲያበረክት መሆኑን ገልጸው፣ በተለያዩ የበለፀጉና በመበልፀግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ያሉ ልምዶችም በርካታ የታለንት ልማትን የሚያግዙ ማኅበራት ጉልህ አስተዋጽኦዎችን እያበረከቱ እንዳሉ ያሳያል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ የሰው ሀብት ልማት ተግባራት ቢኖሩም፣ አብዛኛዎቹ በመንግሥት ወይም በግለሰቦችና በልማት አጋሮች ጥረት እየተከናወኑ ያሉ ናቸው፡፡ እዚህን ጥረቶች ማገዝና ኢትዮጵያን በታለንት ልማት ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ከማድረግ አንፃር በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች በተደራጀ መልኩ ሚናቸውን ሊጫወቱ ይገባል፡፡ ይህንኑ በመገንዘብም አሶሴሽን ፎር ታለንትድ ዴቨሎፕመንት ኢን ኢትዮጵያ ተመሥርቷል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...