Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኢትዮጵያዊው የፈጠራ ባለሙያ የኪፕ ዎኪንግ አፍሪካ ምርጥ 30ዎቹን ዝርዝር ተቀላቀለ

ኢትዮጵያዊው የፈጠራ ባለሙያ የኪፕ ዎኪንግ አፍሪካ ምርጥ 30ዎቹን ዝርዝር ተቀላቀለ

ቀን:

ኢትዮጵያዊው አርቲስት ፋኑኤል ልዑል፣ በኪፕ ዎኪንግ አፍሪካ ከምርጥ 30ዎቹ ዝርዝር (በKeep Walking: Africa Top 30) ውስጥ ከተካተቱት ሰዎች መካከል አንዱ ሆኗል።

ዝርዝሩ ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ጆኒ ዎከርና ትሬስ ቲቪ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ዝርዝሩ ባህላቸውን በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በሚዲያ፣ በፋሽንና በጥበብ ወደፊት የሚያራምዱ የቀጣይ ትውልድ አፍሪካውያን ፈጣሪዎችንና ባለራዕዮችን ያካትታል።

በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተው ምስላዊ አርቲስት ፋኑኤል ልዑል፣ ከአዲሶቹ የአፍሪካ ወደፊት አራማጆች አንዱ ነው ተብሏል። ፋኑኤል የአኅጉሪቱን ታላቅ ታሪክ የሚተርክና የኢትዮጵያ አርበኞችን እንደ ልዕለ ጀግኖች የሚያቀርብ ‘ቅዳማዊ’ የሥዕል መጽሔት ፈጣሪ ነው።

የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሩ ቴምፖ (የC’Kayን ዓለም አቀፍ ድምፅ “Love Nwantiti”ን ያዘጋጀ)፣ በአማፒያኖ የዘፈን ቃና ዝናን ያገኘው ሙሳ ኪያስ፣ የፊልም ዳይሬክተር ሜጂ አላቢ እና በአፕል አይፎን የማስታወቂያ ሥራውና የተወለደበትን ከተማ አክራ በማስተዋወቅ የታወቀው ምስላዊ አርቲስት ፕሪንስ ጊያሲ ይገኙበታል፡፡

የደቡብ አፍሪካው የትሬስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቫላንታይን ጋውዲን ሙቲባ እንዳሉት፣ የአፍሪካን ባህል የሚያስተዋውቁ ፈጣሪዎች አዳዲስ ሥራዎቻቸውን ይዘው እንዲመጡ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡

በውድድሩ የአንጎላ፣ የኮትዲቯር፣ የካሜሩን፣ የኢትዮጵያ፣ የጋና፣ የኬንያ፣ የሞዛምቢክ፣ የናይጄሪያ፣ የሩዋንዳ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የታንዛኒያና የዛምቢያ አርቲስቶችና የፈጠራ ባለሙያዎች የአፍሪካን ባህል ወደፊት በማምጣት ተሳትፈውበታል፡፡

በሙዚቃ ዘርፉ ዲጄ ዲዛየር ከደቡብ አፍሪካ፣ ኢሽ ኬቨን ከሩዋንዳ፣ አቀናባሪው ቴምፖ ከናይጄሪያ፣ ዲ ሄርምስ ከሞዛምቢክ፣ ጉቺ ከናይጄሪያ፣ ሙሳ ኪያስ ከደቡብ አፍሪካ፣ ፖንጎ ከአንጎላ፣ ማሪዮ ከታንዛኒያ፣ ዲጄ ብላክ ከአንጎላ፣ ሩገር ከናይጄሪያ እንዲሁም ይሊም ከአይቮሪኮስት ተሳትፈውበታል፡፡

በጥበብ ዘርፉ ፋኑኤል ልዑል ከኢትዮጵያ፣ ኦቡ ጋቤስ ከአይቮሪኮስት፣ ፕሪንስ ጊያስ ከጋና እና ሱንጊምሊንግ ከታንዛኒያ ናቸው።

በፊልም፣ በፋሽንና በሚዲያ ዘርፍም ውድድሩ ተካሂዷል፡፡ በፓን አፍሪካዊ ዝርዝር ለመካተት፣ የፈጠራ ባለሙያዎች ከተለያዩ አገሮችና ከተለያዩ የፈጠራ መንገዶች ተሳትፈዋል፡፡ የአፍሪካን ባህል ለማሳደግ እያሰሉ ለሚገኙ የፈጠራ ባለቤቶች ዕውቅናን የሰጡት ትሬስ እና ጆኒ ዎከር ናቸው፡፡

ኪፕ ዎኪንግ አፍሪካ ቶፕ 30 የተጀመረው የአፍሪካ የፈጠራ ኢኮኖሚ እያደገ በመጣበት ወቅት ነው። በዩኔስኮ ዘገባ መሠረት፣ የአፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ በ2025 ገቢውን በአራት እጥፍ ማለትም 20 ቢሊዮን ዶላር የሚያደርስ ሲሆን፣ ይህም ለ20 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡ እስከ 2025 የአፍሪካ ዲጂታል ሙዚቃ ሥርጭት ገቢም 500 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...