በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝቱም ያላለቁና እያለቁ ያሉ ስድስት ፕሮጀክቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ከፕሮጀክቶቹ መካከልም ትራፊክ ማኔጅመንት ማዕከል፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር፣ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ ማቋቋሚያ፣ ግራንድ የመኪና ማቆሚያና ሌሎችም ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡
ፎቶ በመስፍን ሰሎሞን