Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ስምምነት ፈጸመች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ስምምነት ፈጸመች፡፡ በስምምነቱ መሠረት በሰዓት 438 ጊጋ ዋት ይደርሳታል ተብሏል፡፡

በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ተገንብቶ እ.ኤ.አ. 2026 ይጠናቀቃል የተባለበት አዲስ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር እንደሚዘረጋ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ አስታውቀዋል፡፡ የመስመር ዝርጋታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ጂቡቲ 100 ሜጋ ዋት ኃይል እንደምትወስድ ታውቋል፡፡

የመስመር ዝርጋታው በኢትዮጵያ በኩል ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 80 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ፣ እንዲሁም በጂቡቲ በኩል ከዓለም ባንክ በተሰጠ የገንዘብ ድጋፍ ተገንብቶ ወደ ሥራ ሲገባ የኤሌክትሪክ ሽያጩ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

በሁለቱም አገሮች ላይ የሚያልፈው የ230 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር በኢትዮጵያ ከሰመራ፣ እንዲሁም በጂቡቲ እስከ ነጋድ የሚረዝም 300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መሆንና ዝርጋታውን ለማስጀመር በቅርቡ ጨረታ እንደሚወጣ አቶ አሸብር አክለው ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ የተደረገው በአዲስ አበባ ከጥቅምት 15 እስከ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ለ16ኛ ጊዜ በተካሄደው የኢትዮጵያና ጂቡቲ ሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ጉባዔ መጠናቀቂያ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብርና በጂቡቲ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲያማ ዓሊ ጌሌ የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተገኙበት ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነት ጂቡቲ ከኢትዮጵያ በሽያጭ የምትወስደውን 243  ጊጋ ዋት በሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ሊያሳድግ የሚችል መሆኑን፣ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመርም ያሰድጋል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በቀጣይ ከታንዛኒያ፣ ከሶማሊያና ከሱዳን ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶች እንደሚፈጸሙ አቶ አሸብር አክለው ተናግረዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1981 የተቋቋመው የኢትዮ ጂቡቲ ሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን በ16ኛው ጉባዔው ሁለቱን አገሮች በሚያገናኛቸው ጉዳዮች በተለይም በትራንስፖርት፣ በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክስ፣ በሰዎች ዝውውር፣ በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ላይ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች