Saturday, July 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበቤት ሠራተኛዋ ላይ ግብረ ሰዶም ፈጽማለች የተባለችው ወጣት 14 ዓመታት ጽኑ እስራት...

በቤት ሠራተኛዋ ላይ ግብረ ሰዶም ፈጽማለች የተባለችው ወጣት 14 ዓመታት ጽኑ እስራት ተፈረደባት

ቀን:

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አልታድ ሚካኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከራይታ ከምትኖርበት ቤት የቤት ሠራተኛዋን በማስገደድ ግብረ ሰዶም የፈጸመችው ወጣት በ14 ዓመታት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ሰጠ፡፡

በተበዳይዋ ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀልና ሌሎች የአካል ጉዳት መፈጸሟ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦ ቅጣቱ የተላለፈባት የ30 ዓመት ዕድሜ ያላት ወጣት ተከሳሽ ሰብለወንጌል እያሱ የምትባል ሲሆን፣ ድርጊቱን የፈጸመችው በ1996 የወጣውን  ወንጀል ሕግ አንቀፅ 630/2/ሀ/ እና /ለ/ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስፍሯል፡፡

  ፍርደኛዋ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555/ሀ/ እና /ለ/ን ድንጋጌዎችንም  በመተላለፍ በፈጸመችው ከባድ የግብረ ሰዶምና ለንፅህና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ወንጀሎችን በመፈጸሟና የወንጀል ሕግ አንቀፅ 590/ሀ/፣ /ሐ/ እና 2/ለ/ን በመተላለፍ ሌሎች ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሷንም የቅጣት ውሳኔው ያስረዳል፡፡

 ፍርደኛዋ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመቸው፣ የግል ተበዳይን በግንቦት ወር 2012 ዓ.ም. አንድ ምሽት ላይ በግድ አረቄ እንድትጠጣ ካደረገቻት በኋላ በቢላ በማስፈራራት ልብሷን ሙሉ በሙሉ በማስወለቅና የራሷንም በማውለቅ ግብረ ሰዶም ፈጽምባታለች፡፡ አፏን በነጠላ በማፈን የሴቶች ፀጉር መሥሪያ ፓይስትራ ሶኬቱን በመሰካት የግል ተበዳይ ድንግልና እንዲገረሰስና ደም እንዲፈሳት በማድረግ ፀያፍ ድርጊት እንደፈጸመችባት ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አብራርቷል፡፡

ፍርደኛዋ የግል ተበዳይን በተደጋጋሚ ጊዜ በቢራ ጠርሙስና በታኮ ጫማ ግንባሯን፣ ጆሮዋን፣ አፍንጫዋን፣ እግሯንና እጇን የመታቻት ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ጆሮዋ እንዲቆስልና እንዲጣመም፡፡ የላይኛው የፊት ጥርሷ እንዲሰበር ከማድረጓም በላይ፣ የፈላ ውኃ በተጎጂዋ ደረት ላይ በመድፋት አካሏ እንዲላላጥ ማድረጓ ተብራርቷል፡፡

በተጨማሪም በቢላ ጀርባዋን በመውጋት ከፍተኛ ጉዳት እዲደርስባት በማድረጓ የግል ተበዳይ በዚህ ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት ሰውነቷ ላይ ጠባሳዎች መፈጠራቸውንም አክሏል፡፡

ተከሳሽ ከቤት በምትወጣበት ጊዜ የግል ተበዳይ ላይ ቆልፋባት የምትወጣ በመሆኑ ድርጊቶቹ በተፈጸሙበት ከመጋቢት 27 ቀን 2012 እስከ ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጎጂዋ በቤት ውስጥ ምግብና የፀሐይ ብርሃን ተከልክላ ለአንድ ዓመት ከሁለት ወር መቆየቷንም ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡ የግል ተበዳይ በወረቀት ጽፋ በመስኮት ቀዳዳ የጣለችውን ወረቀት አንድ ግለሰብ በማግኘቱ የፖሊስ አባላት ለምርመራ በቤቷ በተገኙ ጊዜ ተበዳይን አልጋ ሥር ደብቃት እጅ ከፍንጅ የተያዘች ሲሆን በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዓቃቤ ሕግ ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብና በመመርመር ክስ ሊያስመሠርት የሚያስችል በቂ ማስረጃ በማደራጀት ሦስት የወንጀል ክሶችን መሥርቶ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

ፍርደኛዋ የቀረበባትን ክስ ክዳ ተየተከራከረች ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው፣ የሰነድ፣ ገላጭና ኤግዝቢት ማስረጃዎች አቅርቦ፣ በተከሰሰችባቸው ክሶች ሁሉ ጥፋተኛ በመባሏ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ሌላውን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሽን በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...