Sunday, March 3, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ፖለቲካ አልወድም የሚሉት የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት በደቡብ አፍሪካ ስለተጀመረው ድርድር ሚኒስትሩን እየጠየቁ ነው]

 • እኔ ምልህ ?
 • እ… አንቺ ምትይኝ? 
 • የሚባለው ነገር እውነት ነው?
 • ምን ተባለ?
 • ሰኞ ይጀመራል የተባለው ድርድር ለአንድ ቀን የዘገየው ተደራዳሪዎቹ በቀጥታ ለሕክምና በመሄዳቸው ነው እየተባለ ነው እኮ?
 • የእኛ ተደራዳሪዎች? 
 • እሱን እንድትነግረኝ እኮ ነው የጠየኩህ? 
 • አልሰማሁም… ግን በጭራሽ የእኛ ተደራዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም። 
 • እሱማ የእኔም ጥርጣሬ ሌላ ነው። 
 • አንቺ ማንን ጠረጠርሽ?
 • የታችኞቹን። 
 • አደራዳሪዎቹ አሉ የተባለውስ እውነት ነው?
 • ምን አሉ ተባለ?
 • ተቆጧቸው ይባላል።
 • ምን ብለው?
 • ለድርድር ነው ለሕክምና የመጣችሁት ብለው፡፡ 
 • ይገርማል…!
 • ምኑ?
 • እኛ ሳንሰማ መረጃው እናንተ ዘንድ ነው ያለው። 
 • እያፌዝክብኝ ነው?
 • ኧረ በጭራሽ …ግን እነሱ ምን አሉ ተባለ?
 • በሳንጃው ምክንያት ነው የታመምነው አሉ እየተባለ ነው።
 • በሳንጃው?
 • በሳንጃው …ወይም …በሲንጁ …እንደዚያ መሰለኝ ያሉት።
 • እእእ.. በሲጁ… ገባኝ።
 • ምን ማለታቸው ነው?
 • ወደ ክልሉ ምንም እንዳይገባ በመደረጉ ጤናችን ታውኳል ለማለት ፈልገው ነው። እየተጠቀሙበት ነው።
 • እንደዚያ ነው?
 • አዎ። ክስ ለማቅረብ መሞከራቸው ነው።
 • ቢከሱም ችግር የለውም።
 • እንዴት?
 • እናንተ ጥሩ መከላከያ መልስ አታጡም ብዬ ነዋ?
 • ታመናል ካሉ ምን ማድረግ እንችላለን?
 • ማስረጃ ማቅረብ ነዋ?
 • የምን ማስረጃ? ምን ብለን?
 • የቅርብ ጊዜ አይደለም ብላችሁ።
 • ምኑን ነው የቅርብ ጊዜ አይደለም የምንለው?
 • ሕመማቸውን ነዋ። የቅርብ ጊዜ ሕመም አይደለም ማለት ነው?
 • አይ አንቺ… እሺ የመቼ ነው ስንባልስ?
 • የበፊት ነው ማለት።
 • ከምን በፊት? 
 • ከለውጡ በፊት!

[ክቡር ሚኒስትሩ በቢሯቸው ሆነው ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር በድርድሩ ምን ሊከሰት እንደሚችል ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር እንዲያው ይህ ድርድር ይሳካል ብለው ያምናሉ?
 • በእኛ በኩል ከድርድሩ ምን እንደምንጠብቅ ስላሳወቅን ብዙም አያሳስበንም።
 • እንዴት?
 • ድርድሩን የተቀበልነው መከላከያ ኃይላችን አሁን እየፈጠረ ያለውን ሁኔታ በማጽናት ወደ አጠቃላይ ሰላም እንደሚወስደን በማመን ነው።
 • የእኔ ሥጋት ድርድሩ ባይሳካስ የሚል ነው?
 • እየነገርኩህ እኮ ነው?
 • እ…?
 • ከድርድሩም ሆነ ከወታደራዊ ዕርምጃችን የምንጠብቀው ግብ እንድ ነው። 
 • አሃ… ገባኝ 
 • አዎ። ድርድሩ የምንፈልገውን ውጤት የሚያፈጥን ሰላማዊ መንገድ ነው። 
 • ድርድሩ ባይሳካም የሚፈለገው ውጤት በወታደራዊ መንገድ ይፈጸማል እያሉኝ ነው አይደል? 
 • ይፈጸማል ብቻ ሳይሆን እየተፈጸመ ነው! 
 • ግን እኮ የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎችም ሆኑ ምዕራባዊያኑ ከድርድሩ በፊት አስቸኳይ የግጭት ማቆም ስምምነት እያሉ ነው።
 • የአፍሪካ ኅብረት እንኳ ምዕራባዊያኑን ለማስደሰትና ብያለሁ ለማለት ያህል እንጂ … አቋሙ ከእኛ ብዙም የተለየ አይደለም።
 • ቢሆንም የምዕራባዊያኑ ጫና ቀላል አይደለም ክቡር ሚኒስትር። ግጭት የማቆም ስምምነት ካልተደረሰ አይለቁንም።
 • እኛም ግጭት የማቆም ስምምነት ለመፈጸም ዝግጁ እንደሆንን ደጋግመን ነግረናቸዋል። 
 • ግጭት የማቆም ስምምነት ለመፈራረም በእኛ በኩል ዝግጁ ነን …ይፈለጋል? 
 • አሁን የጀመርነውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማይነካ ከሆነ ችግር የለብንም። ይህንንም በግልጽ አሳውቀናል።
 • እንዴት …ፍጹም አልገባኝም?
 • በሁሉም ክልሎቻችን እንደምናደርገው የፌዴራል መንግሥት ኤርፖርቶችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እንቆጣጠራለን። ይህንን ለማድረግ የማንም ፈቃድ አያስፈልገንም። 
 • አሃ …ስለዚህ ግጭት የማቆም ስምምነት ይህንን መብትና ኃላፊነት የሚገድብ ካልሆነ መንግሥት ይቀበለዋል ማለት ነው።
 • ትክክል፡፡
 • ግን በእነሱ በኩል ይህንን በፍጹም የሚስማሙበት አይመስለኝም። ካልተሰማሙ ደግሞ ድርድሩ ፈረሰ ማለት ነው።
 • የምንጠብቀው ውጤት ተመሳሳይ ነው ያልኩህ ለዚህ ነው። 
 • ከምኑ?
 • ከድርድሩም ከወታደራዊ እንቅስቃሴውም!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...

ምርጫ ቦርድ ፓርላማው ያፀደቀለትን 304 ሚሊዮን ብር አለማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሰኔ 2016 ዓ.ም. በአራት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...