Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዲሲፕሊን ጥሰቶች የታጀበው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ

በዲሲፕሊን ጥሰቶች የታጀበው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ

ቀን:

ከ1990 ዓ.ም. በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የበላይነት ሲመራ የነበረው፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ክለቦች ባቋቋሙት አክስዮን ማኅበር መተዳደር ከጀመረ ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ቀድሞ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ውድድሩ በክለቦች መመራት ይኖርበታል የሚለው ጥያቄም ሲነሳ ከርሟል፡፡

በተለይ በክልሎች የሚደረጉ ጨዋታዎች የዳኝነት ጥያቄ የሚነሳበቸው፣ ክስ የማያጡና በረብሻ የታጀቡ መሆናቸው፣ ውድድሩን ክለቦች ‹‹እራሳችን እናስተዳድረው›› ብለው ጥያቄ እንዲያነሱ አስችሏችዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአክሲዮን ማኅበር በ2012 ዓ.ም. ከተቋቋመ በኋላ ከዲኤስቲቪ ጋር ሙሉ ጨዋታዎችን በቀጥታ ቴሌቪዥን ለማስተላለፍ የሚያስችለውን ስምምነት ከተፈራረመበት ጊዜ ጀምሮ ጨዋታዎችን በቀጥታ ማስተላለፍ መቻሉ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የተወሰኑ ለውጦች እንዲታዩ አስችሎ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ከተሞች በዙር የሚደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች፣ ለከተሞች የሚኖራቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ እንዲሆንና ከተሞቹም በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተዋወቅ ማድረጉን ይገልጻል፡፡

በአንፃሩ አምስተኛ ሳምንቱን የያዘው የ2015 ዓ.ም. የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪየሚየር ሊግ ውድድር ገና ከጅምሩ የዲሲፕሊን ጥሰት በማስተናገዱ፣ ክለቦች ቅጣት እየተጣለባቸው ይገኛል፡፡ ሊጉ በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደር ከጀመረበት ወቅት አንስቶ ዘንድሮ ገና በጠዋቱ በርካታ የዲሲፕሊን ግድፈቶች መታየታቸውን ተከትሎ፣ በክለቦች ላይ ከፍተኛ ገንዝብ ቅጣት እንዲጣልባቸው አስችሏል፡፡

‹‹ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ውድድር በአገራችን እንዲኖር እንጥራለን›› የሚል መፈከር ይዞ የተነሳው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ በየሳምንቱ የጨዋታ መርሐ ግብር የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠምዷል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ፣ በተደረጉ ጨዋታዎች ከዳኞችና ታዛቢዎች  የቀረቡለትን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ፣ የተለያዩ ውሳኔዎች በተካፋይ ክለቦችና ተጨዋቾች ላይ አስተላፍሏል፡፡

በዚህም መሠረት በክለቦች እንዲሁም ከተጫዋቾች ላይ ከ75 ሺሕ ብር እስከ 300 ሺሕ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባችዋል፡፡

ባህር ዳር ከተማ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የአራተኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ፣ የባህር ዳር ደጋፊዎች በመረበሻቸውና ያልተገባ መልዕክት በማስተላለፍ ሁከት በመፍጠራቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ አንቀጽ 66 በተራ ቁጥር 4 መሠረት የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድን 50,000 ሺሕ ብር እንዲሁም የክለቡ ደጋፊ ወደ ሜዳ በመግባት ሁከትና ረብሻ በማስነሳቱ በዚሁ መመርያ አንቀጽ 66 ተራ ቁጥር 3 መሠረት 25,000 ብር በድምሩ ብር 75,000 ብር እንዲከፍል መወሰኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የድሬዳዋ ከተማ ክለብ ከባህር ዳር ጋር ባደረገው የአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች በፈጸመው ተገቢ ያልሆነ ተግባር ምክንያት በተጫዋቹ የተላለፈው ዕገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጫዋቹ በፈጸመው ተጨማሪ ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ አንቀጽ 64 አንድ (ረ) እና ሁለት መሠረት ስድስት ጨዋታ እንዲታገድና 3,000 ብር እንዲከፍል መወሰኑን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ ከአንድ ክለብ ስድስት ተጫዋቾች የተለያዩ የዲሲፕሊን ጥሰቶችን በማከናወናቸው ምክንያት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባችዋል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ ይፋ ካደረጋቸው የዲሲፕሊን ጥሰት ሪፖርት መካከል ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ሌላኛው ሲሆን በሦስተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የአርባ ምንጭ ከተማው ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ ካስመዘገበው የመለያ ቁጥር ውጪ ለብሶ በመገኘቱ 3,000 ሺሕ ብር እንዲሁም ለብሶ ወደ ሜዳ የገባው የመለያ ቁጥር ከተፈቀደው ወጪ በመሆኑ ተጨማሪ 3,000 ብር፣ በድምሩ 6,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

በሌላኛው ሦስትኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከቅድስ ጊዮርጊስ ባደረገው ጨዋታ የሲዳማ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኛ ስለመሳደባቸው ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ 50 ሺሕ ብር ቅጣት ተላልፏል፡፡

ከዚህም ባሻገር  የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ የአትዮ ኤሌክትሪኩ ሔኖክ አየለ ክለቡ ከለገጣፎ ጋር ባደረገው የአራተኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ሃይማኖታዊ መልዕክት የሚያስተላልፍ ጽሑፍ የተጻፈበት ልብስ ከማሊያው ሥር ደርቦ ስለመልበሱ ሪፖርት ተደርጎበታል፡፡ በመሆኑም ተጫዋቹ ባጠፋው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል አንድ አንቀጽ ዘጠኝ የተጫዋች ሌላ ማሳያ በግጥሚያ ወቅት መልበስ እንደማይቻል በሚደነግገው ደንብ ተራ ቁጥር አራትና አምስት መሠረት ተጫዋቹ 3,000 ብር እንዲሁም ክለቡ ብር 10,000 ብር እንዲከፍሉ መወሰኑ ተገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አክሲዮን ማኅበሩ ከየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ስብሰባ አድርጎ ከፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ተከትሎ ከዳኞችና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ፣ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ ክፍል ሦስት ምዕራፍ ሦስት አንቀጽ 65 (ሀ) መሠረት  አምስት ሺሕ ብር እንዲከፍል ወስኗል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ባደረገው የሁለተኛ ሳምንት ኴስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኛ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል፡፡ በመሆኑም የክለቡ ደጋፊዎች ለፈጸሙት ጥፋት ክለቡ በመመርያ ክፍል ሦስት ምዕራፍ ሦስት አንቀጽ 66 ተራ ቁጥር አራት መሠረት የገንዘብ ቅጣት ብር 50,000 እንዲከፍል የተወሰነበት ሳምንት ነበር፡፡

ምንም እንኳን የሊጉ ቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ኖሮት በመላው ዓለም የመታየት ዕድል እየሰፋ ቢመጣም በተጫዋቾች እንዲሁም በደጋፊዎች ላይ የሚታየው የዲሲፒሊን ጥሰት አሳሳቢ መሆኑ እየተነሳ ይገኛል፡፡ ቢዘህም መሠረት የክለብ ድጋፊዎች ማኅበር ተመልካቾችን እንዲሁም ክለቦች ተጨዋቾቻቸው ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባቸው ይነገራል፡፡

የመጨረሻ የሳምንቱ መርሐ ግብር ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት የሚያጠናቅቀው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀምራል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...