Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በሩብ ዓመቱ ወደ ውጭ የተላከው ቡና መጠን ቢቀንስም ከዕቅድ በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ለውጭ ገበያ ያቀረበችው የቡና መጠን ከታቀደው ዕቅድ ያነሰ ቢሆንም፣ የተገኘው ገቢ ከዕቅድ በላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

በሩብ ዓመቱ 20,438.37 ቶን ቡና ለዓለም ገበያ ቀርቦ 426.1 ሚሊየን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ በተጠቀሰው ጊዜ 25,853.43 ቶን ቡና ለማቅረብ ዕቅድ ተቀምጦ እንደነበር ታውቋል፡፡

አገሪቱ ባለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ለውጭ ገበያ ያቀረበችው ቡና መጠን በዚህ ወቅት ከተላከው የመጠን ብልጫ እንደነበረው ያስታወሰው የቡናና ሻይ ባለሥልጣን፣ ከገቢ አንፃር ባለፉት ሦስት ወራት የተገኘው የኤክስፖርት ገቢ የ27.30 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው መሆኑን ገልጿል፡፡

ጀርመን፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ቤልጂየም ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና የገዙ ቀዳሚ ሦስት አገሮች ሲሆኑ፣ በሩብ ዓመቱ ለውጭ ገበያ ከቀረበው የቡና መጠን 21፣ 17ና 13 በመቶ ድርሻውን በቅደም ተከተል እንደሚሸፍኑ ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡

ባለፉት ሦስት ወራት ከተላከው የቡና ዓይነት ሲዳማ፣ ነቀምቴ፣ ይርጋጨፌ በመጠን ከፍተኛውን ደርሻ መሸፈናቸው የታወቀ ሲሆን፣ በመቶኛም የ26፣ 23 እንዲሁም 12 ድርሻ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

በ2013 የበጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ ያገኘችው የውጭ ምንዛሪ 907 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም 248,311 ቶን ቡና በመላክ የተገኘ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት አገሪቱ የቡናን ምርት ለዓለም ገበያ ማቅረብ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ ገቢ ማግኘቷ የሚታወስ  ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ወደ የተለያዩ የዓለም አገሮች ከላከችው 300 ሺሕ ቶን የቡና ምርት 1.4 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም እንዳስታወቁት፣ በተያዘው የበጀት ዓመት 360 ሺሕ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች