Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ነገ በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ለተቀጠረው ውይይት ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ

መንግሥት ነገ በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ለተቀጠረው ውይይት ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ

ቀን:

በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት በነገው ዕለት በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ለሚደረገው የሰላም ውይይት መንግሥት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አረጋገጡ፡፡

አቶ ደመቀ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በየትኛውም ቦታና ጊዜ ቢሆን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ እንደቆየና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረገውም የሰላም ስምምነት ዝግጁነቱን አረጋግጠዋል፡፡ አክለውም የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ፣ ከሁሉም አካላት ጋር ለመሥራት መንግሥት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

በነገው ዕለት የሚደረገው የሰላም ውይይት ላይ መንግሥት ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ባለፈው ረቡዕ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ አምባሳደሩ አንዳንዶች መንግሥት በሚወስደው ‹‹ራስን የመከላከል ዕርምጃ›› ላይ ሐሰተኛ ውንጀላዎችን በማሠራጨት የተጀመረውን የሰላም ውይይት ለማደናቀፍ እየጣሩ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና የግዛት አንድነቷን ለማረጋገጥ በምትወስደው ዕርምጃ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት ጫና እንደማትቀበል መግለጻቸው ታውቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ከዚህ ቀደም የመጀመሪያውን የሰላም ንግግር ጥሪ አስመልክቶ በላከው ደብዳቤ፣ ንግግሩ የሚመቻቸው በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆና ሌሎች ስመጥር አፍሪካውያን መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

ከኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በተጨማሪ ንግግሩን እንደሚያመቻቹ የተገለጹት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንትና በአሁኑ ወቅት የኅብረቱ የሰላምና ደኅንነት ምክር ቤት አማካሪ (ፓነል ኦፍ ዘ ዋይዝ) አባል የሆኑት ፉምዙሌ መላምቦ ንጉካ ናቸው፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት ለማብቃት ለሚደረገው ጥረት በአፍሪካ ኅብረት ከተሰየሙት አሸማጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የሰላም ውይይቱ ላይ መገኘት እንደማይችሉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በተመደበው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ላይ ሥጋት እንዳለው የግብፅ ክለብ አስታወቀ

ክለቡ ዳኛው ‹‹የጡረታ መውጫው የመጨረሻ ጨዋታ›› መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል የ2023...

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ከሕገ መንግሥቱ ውጪ በተግባር እንደሌለ ፓርቲዎች ተናገሩ

ብልፅግና ስለመድበለ ፓርቲ ለውይይት ጥሪ ቢደረግለትም አልተገኘም በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ...

ሒዩማን ራይትስዎች ያወጣው ሪፖርት የዕርቅና የምክክር ሒደቱን እንደሚያደናቅፍ መንግሥት አስታወቀ

በትግራይ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት የዘር ማፅዳት እየተካሄደ...

የመጪው ዓመት አገራዊ በጀት ሁለት በመቶ አድጎ ለፓርላማ ተመራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም. በጀት እየተጠናቀቀ ካለው በጀት...