Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከጠየቀው በጀት 75 በመቶው ተፈቀደ

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከጠየቀው በጀት 75 በመቶው ተፈቀደ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሊያካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያነት ከጠየቀው 541.3 ሚሊዮን ብር በጀት ውስጥ 75.7 በመቶው ማለትም 410.1 ሚሊዮን ብር እንደተፈቀደለት አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በዋሽንግተን ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው።

ቦርዱ 3.1 ሚሊዮን መራጮች እንደሚሳተፉበት ለሚጠበቀው ህዝበ ውሳኔ የተፈቀደለት በጀት ከጠየቀው በ131.3 ሚሊዮን ብር ያነሰ ነው።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ቦርዱ የበጀት እቅዱን ያዘጋጀው ከዚህ ቀደም ካካሄዳቸው ምርጫዎች ተሞክሮ በመነሳትና ተጨባጭ የገበያ ሁኔታውን በመመልከት መሆኑን አስረድተዋል።

ይሁንና በጀቱን የሚፈቅደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “አንዳንድ” የቦርዱ ጥያቄዎች “የተጋነኑ” ናቸው ፣ እንዲሁም “በመረጃ ላይ የተደገፉ አይደሉም” በሚሉ ምክንያቶች ቦርዱ ከጠየቀው ያነሰ በጀት መፍቀዱን ተናግረዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን አክለውም፣ “ስራውን እያከናወንን ስንሄድ [የበጀት] እጥረት የሚያጋጥም ሆኖ ከተገኘ ግን ተጨማሪ በጀት እንጠይቃለን” ብለዋል።

ይሄንን ተከትሎም ቦርዱ የተፈቀደለትን በጀት በመጠቀም ህዝበ ውሳኔውን የወጪ ቅነሳ አማራጮችን በመጠቀም ለማካሄድ ማቀዱንም ገልጸዋል።

ቦርዱ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሊያካሂድ ባሰበው በዚህ ህዝበ ውሳኔ በደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች በክልልነት ለመዋቀር ያሳለፉት ውሳኔ ላይ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...