Tuesday, December 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ እንኳን ደስ አለዎት እያለ ወደ ቢሯቸው ገብቶ በጨዋታና መረጃ በመፈለግ መካከል ያለ ጥረት እያደረገ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር እጅግ የሚያስደስት ነገር ነው። እንኳን ደስ አለዎት፡፡
  • ምኑ? ምን ተገኘ?
  • ባለፈው የነገሩኝ ስልት በጣም ውጤታማ ነው። 
  • የቱ ስልት? 
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ያጫወቱኝ ነዋ? ለማንኛውም በኃይል ከያዙት አካባቢ እግሬ አውጪኝ ብለዋል።
  • እውነት፡፡
  • አዎ። አልሰሙም እንዴ?
  • እኔ ምንም የሰማሁት ነገር የለም። 
  • የምርዎትን ነው ክቡር ሚኒስትር? 
  • አልሰማሁም ስልህ? 
  • የካቢኔ አባል ሆነው ምንም ካልሰሙ ተግባራዊ የሆነው ስልት በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚፈጸም ነው ያሰኛል።
  • የቱ ስልት? 
  • ባለፈው የነገሩኝን የውጊያ ስልት ማለቴ ነው። 
  • የውጊያ ስልት? እኔ ነኝ የነገርኩህ?
  • አዎ!
  • ምን ብዬ?
  • ምታ በዝምታ!
  • በጭራሽ አላስታውስም… እርግጠኛ ነህ እኔ ነኝ የነገረኩህ? 
  • አሃ …ገባኝ ገባኝ!
  • ምን?
  • በዘዴ እየነገሩኝ እንደሆነ ገባኝ። 
  • በዘዴ የገባህ ምንድነው? 
  • ማስተካከያ እንደተደረገበት።
  • ምኑ?
  • ምታ በዝምታ። 
  • ምን ተባለ?
  • ምታ በዝምታ ጠላት እስኪምታታ፡፡
  • ኦሆሆ… አንተ መቼም…
  • እውነቴን ነው እንደዚያ እኮ ነው ያደረጋቸው?
  • ምኑ?
  • ምቱ!
  • እንዴት? 
  • መጀመሪያ ለቀን ነው የወጣነው አሉ።
  • እሺ፡፡
  • ቀጥሎ ደግሞ ተሸንፈን አይደለም ስትራቴጂክ የቦታ ለውጥ ነው አሉ።
  • ማን ተሸንፋችሁ ነው አለ? 
  • እሱን እኮ ነው የምልዎት፡፡
  • እሺ፡፡ 
  • ቀጥሎ ደግሞ መንግሥት ራሱ መግለጫ አለመስጠቱ የሚያረጋግጠው ተሸንፈን አለመውጣታችን ነው አሉ።
  • መንግሥት አሁንም በዝምታው ሲቀጥል ደግሞ ምን አሉ መሰሎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እህ…
  • እንገናኛለን፡፡
  • ኪኪኪ… ወይ አንተ!
  • በዚህ ከቀጠሉ ወደፊት ምን የሚሉ ይመስልዎታል? 
  • እ…?
  • እጅ በእጅ!
  • እጅ በእጅ ምን?
  • እጅ በእጅ ይዋጣልን!

  [ክቡሩ ሚኒስትሩ ከዓብይ የሰላም ኮሚቴው ጋር ድርድሩን የተመለከተ ሪፖርት ተቀብለው ተጨማሪ መረጃ እየጠየቁ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በእኛ በኩል ማድረግ የሚገባንን ዝግጅት አድርገናል ነገር ግን …
  • ነገር ግን ምን?
  • ክቡር ሚኒስትር ሌላኛው ተደራዳሪ አቋሙን የቀየረ ይመስላል? 
  • እንዴት? ምን ተፈጠረ? 
  • እኛን ቅርቃር ውስጥ ለማስገባት አልሞ የዘመን መለወጫ ቀን ላይ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አሳውቆ አልነበር?
  • አዎ። 
  • የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነትን መቀበል ብቻ ሳይሆን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመደራደርም ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ቅድመ ሁኔታ የሌለው ጥሪ ነበር ያቀረበው። 
  • አዎ። አስታውሳለሁ፡፡
  • አሁን ወደ ድርድር ለመግባት ጥረቶች ሲጀመሩ ወደ ቀደመ አቋሙ ተመልሷል።
  • ወደ ቀደመ አቋሙ ማለት? 
  • የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነትን ብቀበልም ዋና አደራዳሪውን አልቀበልም እያሉ ነው። 
  • እንደዚያ አሉ?
  • እሱ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል ያስቀመጣቸውን ሁሉንም ቅድመ ሁኔታዎች ዳግም በቅድመ ሁኔታነት እያቀረበ ነው።
  • እርግጠኛ ነህ? 
  • አዎ። ተደራዳሪ ተብለው የተመደቡት ሰዎዬ ናቸው በይፋ የተናገሩት።
  • እንደዚያ ከሆነ እኚህን ተደራዳሪ መንግሥት እንደማንቀበል ለአደራዳሪዎቹ እሳውቁ፡፡
  • እንዴት? ለምን ብለው ቢጠይቁንስ? 
  • በመጀመሪያ ሕጋዊ ዕወቅና ያለው የክልል መንግሥት ባለመኖሩ ድርድሩን የምናደርገው ከክልሉ ፓርቲ ጋር እንደሆነ አሳውቋቸው። 
  • ጥሩ። ከዚያ በኋላስ?
  • ሰውዬው የክልሉ ፓርቲ አባል እንዳልሆኑ ጠቅሳችሁ እንደማንቀበል አሳውቁ። 
  • እሺ። ጥሩ መላ ነው። 
  • ሌላ የገጠማችሁ ችግር አለ?
  • ትልቅ ችግር አለ ክቡር ሚኒስትር። 
  • ምንድነው? 
  • በድርድሩ መሳተፍና ሚና እንዲኖራቸው የሚፈልጉ አገሮች ቁጥር እየጨመረ ነው።
  • የትኞቹ አገሮች ናቸው። 
  • የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አለ። አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረትም መሳተፍ አለብን እያሉ ነው።
  • የተባበሩት መንግሥታት አይበቃም እንዴ? 
  • እኛ የሌለንበት ድርድር አይታሰብም እያሉ ነው። እነሱን ተከትሎ ደግሞ ሌሎች አገሮችም ጥያቄ አቅርበዋል።
  • የትኞቹ አገሮች?
  • ሩሲያ፣ ቻይናና የዓረብ አገሮች ናቸው። በዚህም ምክንያት ማን ታዛቢ መሆን አለበት የሚለው ላይ ስምምነት ጠፍቷል።
  • ሌላ ድርድር ገጥሞናል ማለት ነዋ?
  • አዎ።
  • ጥሩ ነው፡፡
  • እንዴት?
  • እነሱ እስኪስማሙ እኛ ፈትተን እንጠብቃቸዋለን።
  • ምኑን ፈትተን?
  • የውስጥ ችግራችንን!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ለካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ስድስት የቦርድ አባላት ተሾሙ

  ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

  የትጥቅ  መፍታት ሒደትና የሰላም እንቅፋቶች

  የትግራይ ተራሮች ከጦር መሣሪያ ጩኸት የተገላገሉ ይመስላል፡፡ በየምሽጉ አድፍጠው...

  በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

  ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በክልሎችም ሊቋቋም ነው በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ...

  የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚመራና የሚቆጣጠር ራሱን የቻለ ተቋም የመመሥረት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

  የኢንሹራንስ (መድን) ዘርፍን የመቆጣጠርና የመከታተል ኃላፊነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...

  ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በበይነ መረብ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ

  በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሐ ግብሮች የሚመረቁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...