- ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉንና ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማምሻውን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም ፣ ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም ሆኗል፡፡
ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አለመደረጉንና ተሽከርካሪዎቹ በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ መሠረት ቤንዚን በሊትር 41.26 ብር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 40.86 ብር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን፣ ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አለመደረጉን ንግድና ቀጠናዊ ትስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
- Advertisement -
- Advertisement -