Tuesday, December 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  እግዜር ፖለቲካው

  ትኩስ ፅሁፎች

  እግዜር ፖለቲካው ዝም – ዝም እግዜር ፖለቲካው

  እንጃ ሌላውን፣ እኔን ግን ሲገርመኝ ይኼ ዝምታው

  እንዲህ ያለ ዝምታ ምንድን ነው?

  ***

  ዝም ማለት እንዲህ ዝም መደበት

  አላይነቱ ዓይነት

  አለው ከሚባለው አንጀቱ አንፃር አባትነት

  እማይረዱት እማይረዱት ምስጢር።

  **

  እንዴት ጭጭ እንዲህ ዝም ብሎ ማየት!?

  ዘመናዊ ነፍጠኛ ሲጫወትበት

  ሰው አጋድሞ ይባርክ ብሎ ሲያወራርድ ሲያርድ

  ቆዳውን ገፍፎ ሲገደግድ

  ግድግድ ነቅሎ በፖለቲካ ገቢያ ሲነግድ!?

  **

  አብሮም ያጠባ ጡትም ሲጎምድ ሙዳ ሥጋ ይመስል

  ከወለደ ማሕፀን ስለት ሲሰድ ስምጥ!!

  ነገሩን ያየ ቀርቶ የሰማን የሚሰቀጥጥ፣

  እንዴት ይቻላል ዝም ማለት ዝም አለመታመም

  ላጤነው የእግዜሩ ፖለቲካ ሲገርም።

  • ሰይፉ መታፈሪያ ‹‹የተጉዋጎጠ ልብ››

  ***

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች