Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት ለመፍታት በሚያስችል የአሠራር ማዕቀፍ ላይ መወያየታቸውን የኬንያው ፕሬዚዳንት ተናገሩ

የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት ለመፍታት በሚያስችል የአሠራር ማዕቀፍ ላይ መወያየታቸውን የኬንያው ፕሬዚዳንት ተናገሩ

ቀን:

በቅርቡ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዊሊያም ሩቶ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ይጠቅማሉ በተባሉ የድርድር ማዕቀፎች ላይ መወያየታቸውን ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ሩቶ ዓርብ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ከፈረንሣይ የዜና አውታር ፍራንስ 24 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት ያስችላሉ ተብለው በተለዩ ማዕቀፎችና አሠራሮች ላይ፣ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማ ፎዛ፣ ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።

‹‹ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ለመቅረፍ በምንችልበት ማዕቀፍና አሠራር ላይ ከመሪዎቹ ጋር ውይይት አድርገናል። በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ሥር በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆና በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ እንዲሁም በሁሉም ተዋናዮች ድጋፍ፣ ሁለቱን ወገኖች በተቻለ ፍጥነት ወደ ጠረጴዛው ማምጣት መቻል እንዳለብን እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም ጦርነቱ የሰው ልጆችን ሕይወት ዋጋ እያስከፈለ ነው። ይህ ጦርነት የአፍሪካ ቀንድንም ወደ ቀውስ የሚያንሸራትትና በጣም ደካማ  የሚያደርግ ነው፤›› ብለዋል።

ኢትዮጵያና ኬንያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና የሚገኙ ሁለት ትልልቅ ኢኮኖሚዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንገዳገድ ኬንያንም ያዳክማታል፣ ስለሆነም በዚህ የሰላም ሒደት መሳተፍ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው፤›› ብለዋል።

በዚህም ምክንያት የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው ሥልጣን በተረከቡበት ወቅት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፣ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት የተጀመረውን ጥረት እንዲቀጥሉ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ዊሊያም ሩቶ ለፕሬዚዳንትነት መወዳደራቸውን በመንቀፍ ለተቀናቃኛቸው ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን ኡሁሩ ኬንያታ፣ በኢትዮጵያና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉትን ግጭቶች ለመፍታት እንዴት የሰላም ልዑክ አድርገው ሊሾሟቸው እንደቻሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያም ሆነ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተጀመረውን የሰላም ጥረት ቢያስቀጥሉ መልካም ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ በማመናቸው እንደሆነ ተናግረዋል። 

‹‹እሱ (ኡሁሩ ኬንያታ) ለፕሬዚዳንትነት ሳደርግ የነበረውን ውድድር ደገፈም አልደገፈ ያ አሁን ያለፈ ሒደት ነው። እኔ አሁን የኬንያ ፕሬዚዳንት ነኝ፣ የመወሰን ኃላፊነት ያለኝ ሰው ነኝ። ስለዚህ እሱ የጀመረው ጥረት እንደታሰበው ባይሄድና ወይም ነገሮች የሚበላሹ ከሆነ ወደ ጠረጴዛ ነው የሚመጣው። እኔ ለምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ጥሩ ነገር እንዲመጣ እፈልጋለሁ፤›› ብለዋል።

ቀደም ብለው ተመሳሳይ ቃለ ምልልስ ከአልጄዚራ ጋር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ በኢትዮጵያ ከሚታየው የሰላም መደፍረስ አኳያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) አመራር እንዴት እንደሚመለከቱት ተጠይቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንደሚለውጡ እምነት እንዳለቸው ገልጸው ነበር።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያን የአኅጉራዊ የነፃ የንግድ ቀጣና ተሳታፊ ለማድረግ ድርድር እየተደረገ መሆኑ ተነገረ

ኢትዮጵያ ወደ ትግበራ ለማስገባት ዘግይታበታለች ተብሎ የሚነገረውን የአፍሪካ ነፃ...

ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞችን ለመቀበል መዘጋጀቷን አስታወቀች

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኦማን ጋር አዲስ ስምምነት ላይ መድረሱን...

ገዳ ቢዝነስ ግሩፕ በቅርቡ ለሚጀምረው እርሻ ከ500 ሔክታር በላይ መሬት አዘጋጅቻለሁ አለ

ገዳ ስታር ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማኅበር በቅርቡ አስጀምራለሁ ላለው...

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...