Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በቴሌ ብር የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት 164.3 ሚሊዮን ብር ብድር መለቀቁ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኩባንያው ስማርት ሲቲዎችን ለማቋቋም ከከንቲባዎች ጋር በንግግር ላይ ነው

ከሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ላይ በዋለው የቴሌ ብር ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት፣ ከ164.3 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መለቀቁ ተገለጸ፡፡

የቴሌ ብር ደንበኞች ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሠረት በቀን 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር በቀረበበት የቴሌ ብር ‹‹መላ›› የአነስተኛ ብድር አገልግሎት፣ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 133,101 ያህል አገልግሎት ደንበኞች ከ164.3 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ወስደዋል ተብሏል፡፡

ቴሌ ብር ‹‹እንደ ኪሴ›› የሚል ስያሜ በተሰጠውና ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ ደንበኞች የቴሌ ብር ሒሳባቸው ከሚገዙት ዕቃ በታች ከሆነ፣ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ በሚከፈልበትና ደንበኞች ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሒሳባቸው ላይ ተቀናሽ በሚደረግበት አገልግሎት፣ 24.1 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈጸሙን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደንበኞች በቴሌ ብር ካላቸው የገንዘብ መጠን ላይ በወለድና ያለ ወለድ የቁጠባ አማራጮች መቆጠብ እንዲችሉ በቀረበው የቴሌ ብር ‹‹ሳንዱቅ››  የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት፣ 71,442 በሚደርስ አገልግሎት ደንበኞች ከ205.8 ሚሊዮን ብር በላይ የአነስተኛ የቁጠባ አገልግሎት ተገልጋይ መሆናቸውን ኩባያው ገልጿል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሶስቱም የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች (በአነስተኛ ብድር፣ በኦቨርድራፍትና በቁጠባ) በአጠቃላይ በዓመት ውስጥ 12.8 ሚሊዮን ደንበኞችን ተጠቃሚ በማድረግ ከ108 ሚሊዮን በላይ የግብይት ቁጥርና ከ19.5 ቢሊዮን ብር በላይ መጠን ያለው የብድርና የቁጠባ ግብይት ለማከናወን ማቀዱን፣ ከዚህ ቀደም መገለጹ ይታወሳል፡፡

ኩባያው እስካሁን ድረስ 24 ሚሊዮን የቴሌ ብር ደንበኞችን በማፍራት 65.6 ቢሊዮን የገንዘብ ዝውውር መፈፀሙን ገልጾ፣ ከ39 የተለያዩ አገሮች ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ዶላር የቴሌ ብር ሃዋላ አገልግሎት መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮ ቴሌኮም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የስማርት ሲቲዎችን ለመገንባት ከከንቲባዎች ጋር ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቆ፣ በዚህ ወቅት ቦታዎች ተመርጠው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውንና በቅርቡ ለማሳያ የሚሆኑ ሥራዎች ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡

ስማርት ሲቲ በዋናነት በከተሞች ዘወትር የሚደረጉ አገልግሎቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና የመረጃ ትንተናዎችን በመጠቀም፣ የዜጎች ኑሮ ከመደበኛው የቴሌኮም አገልግሎት ያለፈ መፍትሔ ሆኖ የሚቀርብት መንገድ መሆኑ ይነገራል፡፡

ከዚህ በሻገር የግብርና ሚኒስቴር ከማዕከል ሆኖ በአጠቃላይ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ያሉ ሰብሎች ያሉበት ደረጃ ለማየት የሚቻልበትን የስማርት አግሪካልቸር ሥራ ይፋ እንደሚያደረግ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች