Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካ ዓቃቤ ሕግ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተካተቱበት የ250 ሚሊዮን ዶላር የማጭበርበር ክስ መሠረተ

የአሜሪካ ዓቃቤ ሕግ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተካተቱበት የ250 ሚሊዮን ዶላር የማጭበርበር ክስ መሠረተ

ቀን:

የአሜሪካ ዓቃቤ ሕግ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተካተቱበት በ47 ግለሰቦች ላይ የ250 ሚሊዮን ዶላር የማጭበርበር ክስ መመሥረቱን አስታወቀ፡፡

የአገሪቱ ዓቃቤ ሕግ መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በድረገጹ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ለሕፃናት አልሚ ምግብ ለማቅረብ በሚል ሰበብ ያደረጉት የማጭበርበር ተግባር መሆኑን አስታውቋል፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ተጭበረበረ የተባለው ገንዘብ በአሜሪካ የወረርሽኝ ታሪክ የተጭበረበረ ትልቅ ገንዘብ መሆኑን ዓቃቤ ሕግ ባወጣው መግለጫ ተጠቁሟል፡፡

ከተከሰሱት 47 ግለሰቦች መካከል ‹‹ፊዲንግ አወር ፊውቸር›› የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሚ ቦክ የተባሉ ግለሰብና ቤካም አዲሱ፣ መርዳሳ፣ ሃና ማረከኝ የተባሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም የተካተቱበት ሲሆን የተከሰሱበት ገንዘብ በወረርሽኙ ወቅት ሕፃናትን ለመመገብ የሚያገለግልና በማጭበርበር የተገኘ ገንዘብ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

ክሱ እንደሚያሳየው ለሕፃናቱ ምግብ ይሄዳል ተብሎ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ በጣም ውስኑ ብቻ ለተፈለገው ዓላማ የዋለ ሲሆን፣ ቀሪውን ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተከፈተ ድርጅት ስም መባከኑን፣ ለቅንጡ ተሽከርካሪዎችና በጉዞ መልክ ወጪ መዋሉ ተጠቁሟል፡፡

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሕጻናትን ለመመገብ በአቅራቢዎች በኩል መቅረብ የነበረበትን ምግብ የሚገዛው ገንዘብ፣ ከአሜሪካው የግብርና ሚኒስቴር በኩል የቀረበ ሲሆን፣ በሚኒሶታ የአሜሪካው የትምህርት ሚኒስቴር በለጋሽ ድርጅቶች አማካይነት ለማከፋፈል ከተመዘገቡት ውስጥ ይህ ተከሳሽ ድርጅት ምግብን ለሕጻናት እንዲደርስ በአከፋፋይነት የተመዘገበ ነበር፡፡

በወረርሽኙ ተማሪዎችን በምገባ ማዕከል ለመመገብ ያስችላል በሚል የቀረበውን ገንዘብ ተማሪዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት ምገባ ማዕከል ባለመሄዳቸው፣ ተከሳሾቹ ባቋቋሙት ድርጅት ስም የውሸት ደረሰኝና ሐሰተኛ የሕጻናት ዕድሜና የስም ዝርዘር መዝግበው በማስቀመጥ፣ በየቀኑ እንደሚመገቡ በማስመሰል በሐሰት ማቅረቡን በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ከአንድ ዓመት በፊት የፌዴራል የምርመራ ቢሮ ባቀረበው አቤቱታ፣ ቢሮው 20 ወራትን በፈጀው የምርመራ ሥራው የድርጅቱን ቢሮና የዋና ሥራ አስፈጻሚዋን መኖሪያ ቤት ጭምር ፍተሻ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም በቁጥር በአንድ ጊዜ 120 ሚሊዮን ሕጻናትን መመገብ የሚችል ምግብ ወጪ እንደተደርገ ተደርጎ በሐሰት ተመዝገቦ መገኘቱን በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ተጠርጣዎቹ ከተፈረደባቸው ለረዥም ዓመታት በእስር ቤት እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...