የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓም በተደረገው የምርጫ ፉክክር ተፎካካሪያቸውን በከፍተኛ ድምጽ በማሸነፍ ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፈዋል።
ብቸኛ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡትን አቶ ኦዴኮ አብዲን በማሸነፍ የተመረጡት ወ/ሮ መሰንበት ከ420 በላይ ድምጽ ማግኘታቸው ታውቋል።
ምክር ቤቱ እስከመጨረሻው ጥቂት ቀናት ድረስ እጩ ተወዳዳሪዎችን ባለማሳወቁ ትችት ሲዘነዘርበት የነበረ ሲሆን፣ በመጨረሻ ላይ አቶ ኤዴኮ አብዲ ተወዳዳሪ መሆናቸው ታውቆ ነበር። ወ/ሮ መሰንበት ምክር ቤቱን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ይመራሉ።