የእንግሊዝ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ሥርዓተ ቀብር ሰኞ መስከረም 9 ቀን ሲፈጸም ከተገኙት የዓለም መሪዎች መካከል የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች የተጓጓዙበት መንገድ ለአገራዊ ክብራቸው በሚመጥን መልኩ አልተፈጸም ያስባለው በአንድ ተሸከርካሪ እንዲጓዙ መደረጉ ነው፡፡ ይህም አፍሪካውያን በዓለም ያላቸውን ስፍራ ያሳየ ነው ተብሏል። በቀደመው ጊዜ ከስድስት አሠርታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ሥርዓተ ቀብር ሲፈጸም የተገኙት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከግንባር ቀደም የዓለም መሪዎች መካከል ከእነ ፕሬዚደንት ደጎል ጋር ከመጀመርያው ረድፍ ከቆሙት ሦስት መሪዎች አንዱ እንደነበሩ ፎቶው ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ፎቶ የዘንድሮ የአፍሪካ መሪዎች ወደ ንግሥቲቷ ሥርዓተ ቀብር በመለስተኛ ተሸከርካሪ ተጭነው ሲሄዱ ያሳያል።
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -