Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ዓርብ ይጫወታል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ዓርብ ይጫወታል

ቀን:

  • የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ መስከረም 20 ይጀምራል

በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዕውቅና ካላቸው የውድድር መድረኮች መካከል የወዳጅነት ጨዋታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ለረዥም ዓመታት በፊፋ የወዳጅነት ጨዋታ መርሐ ግብር መሳተፍ ሳይችል የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ)፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የፕሮግራሙ አካል ሆኖ የወዳጅነት ጨዋታዎችን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሆነው እንዲቀጥሉ የሁለት ዓመት ኮንትራት ከፌዴሬሽኑ ጋር የተፈራረሙት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ፣ ፊፋ ወቅቱን ጠብቆ በሚያከናውናቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች መሳተፍ ይችሉ ዘንድ የመረጧቸውን ተጨዋቾች ዝርዝር ይፋ አድርገዋል፡፡

በፊፋ የውድድር ፕሮግራም መሠረት ብሔራዊ ቡድኑ መስከረም 13 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል፡፡ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለጨዋታው የመረጧቸውን 23 ተጨዋቾች በማሳወቅ ዝግጅት ጀምረዋል፡፡

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጨዋቾች መካከል በረኞች በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰኢድ ሀብታሙ አዳማ ከተማ፣ ዳንኤል ተሾመ ድሬዳዋ ከተማ ሲሆኑ፣ ተከላካዮች አሥራት ቱንጆ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሱሌማን ሐሚድ፣ ሔኖክ አዱኛ፣ ረመዳን የሱፍና ምኞት ደበበ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጌት ጋትኩት ሲዳማ ቡና፣ አስቻለው ታመነ ፋሲል ከተማና ፍሬዘር ካሳ ሀድያ ሆሳዕና ሆነዋል፡፡

አማካዮች ጋቶች ፓኖም ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አማኑኤል ዮሐንስ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሽመልስ በቀለ ከግብፁ ኤል ጉውና፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮና ታፈሰ ሰለሞን ፋሲል ከነማ፣ መሱድ መሐመድ አዳማ ከተማና ከነዓን ማርክነህ መቻል ናቸው፡፡ አጥቂዎች በረከት ደስታ መቻል፣ ዳዋ ሁቴሳ አዳማ ከተማ፣ ይገዙ ቦጋለ ሲዳማ ቡናና  ቸርነት ጉግሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ፣ አሥር አገሮች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በወጣው የምድብ ድልድል በምድብ አንድ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ተደልድለዋል፡፡ በምድብ ሁለት ደግሞ ኡጋንዳ፣ ጂቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳንና ቡሩንዲ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ውድድሩ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በአልጀሪያ አስተናጋጅነት የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ለሚከናወነው አኅጉራዊ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሁለት ቡድኖችን ማለትም በውድድሩ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁትን ለመለየት ያለመ ስለመሆኑ ጭምር ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...