Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሉ አምበል ሉቺያኖ ቫሳሎ (1927-2015)

የሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሉ አምበል ሉቺያኖ ቫሳሎ (1927-2015)

ቀን:

የአፍረካ እግር ኳስ ዋንጫ ሲታወስ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስማቸው ቀድሞ ከሚታወሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለተኞች መካከል ስሙ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችና አሠልጣኝ እንዲሁም የሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሉ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሉቺያኖ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ትውልዱ በኤርትራ በ1927 ዓ.ም. እንደሆነ የሚነገርለት ሉቺያኖ ቫሳሎ፣ እሱና ወንድሙ ኢታሎ ቫሳሎ የዚያ ትውልድ አካል ከመሆናቸው ባሻገር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ሁሌም ከፊት የሚያስቀድማቸው በታሪካዊ ውለታቸው አይረሴ ስለመሆናቸው ጭምር ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡

ሕልፈቱ እስከተሰማበት ጊዜ ድረስ በጣሊያኗ ሊዶ ከተማ የኖረው ሉቺያኖ ቫሳሎ፣ በእግር ኳስ ሕይወቱ ቀድሞ ድሬዳዋ ጥጥ ማኅበር (ወደ ኋላ ላይ ድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ) እንዲሁም ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመጫወት ይታወቃል፡፡

በዘመኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ሆኖ ባደረጋቸው በተለያዩ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል፣ ከቡድኑ ጋር ታሪካዊ ተብሎ እስካሁን የሚጠቀሰውን ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ከፍ ያደረገ ድንቅ እግር ኳሰኛ እንደነበርም በግለ ታሪኩ የቀረቡ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡

በ1954 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተደረገው የ3ኛ አፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ግብፅን 4 ለ2 ኢትዮጵያ ስታሸንፍ ወሳኝ ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ፣ እግር ኳስ እንዲህ እንደ አሁኑ ባልዘመነበት በዚያን ዘመን ከተጨዋችነት ሕይወቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በማሠልጠን ታሪክ የሚያስታውሰው ድንቅ እግር ኳሰኛ ነበር፡፡

ታላቁ የእግር ኳስ ሰው ሉቺያኖ ቫሳሎ ባሳለፍነው ሳምንት በ87 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተከትሎ ብዙዎች ሐዘናቸውን እየገለጹለት ይገኛል፡፡ የሉቺያኖ ቫሳሎ ሥርዓተ ቀብር በሚኖርበት ጣሊያን ሊዶ ከተማ ቅድስት ሞኒካ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...