Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሞተር ሳይክል ጋላቢዎችና የትራፊክ ሕግ ጥሰታቸው

የሞተር ሳይክል ጋላቢዎችና የትራፊክ ሕግ ጥሰታቸው

ቀን:

የሞተር ሳይክል ግጭት የሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍና በሕክምና ወጪ ከፍተኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡     

 በሞተር ሳይክል በሚደርስ ግጭት የሚደርስ የሞት አደጋ በመኪና አደጋ ከሚደርሰው አምስት እጥፍ መሆኑን ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አስከፊ አደጋ በማድረስም አሥር እጥፍ ይልቃል፣ በግጭቱ የደረሰ ጉዳትን ለማከምም ከፍተኛ ወጪ ያስወጣል፡፡  

የሞተር ሳይክሎች ጉዳት አስከፊ የሆነበት  ምክንያት ደግሞ  መኪኖች  ያሏቸው የደኅንነት መጠበቂያ ቁሶች ስለሌሏቸው ነው፡፡  ሞተር ሳይክል መንዳት ከመኪና ይልቅ የአደጋ ተጋላጭነቱ ከፍተኛ በመሆኑ የሚደረጉ የደኅንነት መጠበቂያ መጠቀሙ እንደሚበጅ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አንዱ የደኅንነት መጠበቂያ ዓለም አቀፍ የሔልሜት ሕጎችን መተግበር ነው፡፡ ከአልኮል አለመታቀብ ደግሞ ሌላው የትራፊክ አደጋ አጋላጭ ሁኔታ ነው፡፡ ሞተር ጋላቢዎች የአደጋ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ‹‹ሔልሜት ማድረግ፣ ለፍጥነት ገደቦች መገዛትና አልኮል አለመጠቀም›› ዋነኛ አማራጭና መትፍሔ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በአዲስ አበባና ሞተር በብዛት ጥቅም ላይ በሚውልባቸው የክልል ከተሞች  ሔልሜት የማጥለቅ ግዴታ መተግበር መጀመሩ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ሳይክል ጋላቢዎች አጠቃቀም ሲታይ በእጅጉ አስፈሪና ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ መንገዶች ሲዘጋጉ በጠባብ ቦታዎች እየተሽሎኮሎኩ መሄድ፣ የትራፊክ መብራት መጣስና ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ከሚታዩት ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ አካሄዳቸውም የትራፊክ አደጋን ከማስከተሉ በተጨማሪ ለእይታም የሚዘገንን ተግባር መሆኑ አልቀረም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ሳይክሎች በሁለት ዓይነት መንገዶች አገልግሎት እንደሚሰጡ ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ ያገኘነው ያመለክታል፡፡

እነዚህ ተሽከርካሪዎች በመለያ ቁጥር ሁለትና ሦስት ለሰውና ለዕቃ ለማጓጓዝ ፈቃድ አውጥተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ወደ ሥራ ሲገቡም የትራፊክ ማኔጅመንት የሚቆጣጠርባቸው ሦስት መሠረታዊ የቁጥጥር ሥራዎች አሉት፡፡ እነዚህም ሔልሜት፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፈቃድ፣ ጂፒስ ሟሟላት ግዴታ እንዳለባቸው ይገልጻል፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ጌታቸው ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በከተማዋ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች መሠረታዊ ችግሮቻቸው ለመንገድ ትራፊክ ደንብና ሕግ ተገዥዎች አይደሉም፡፡ ከተለያዩ የአሽከርካሪዎች ዓይነቶች መካከል የትራፊክ ደንብና ሕግ ከሚጥሱት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች መሆናቸውን አቶ ቢንያም ተናግረዋል፡፡ በምሳሌነትም ያነሱት የትራፊክ መብራት ጥሶ የመሄድ፣ ዚግዛግ መሄድ፣ በመኪና መሀል እየተሽሎኮሎኩና በተቃራኒ አቅጣጫዎች መጓዝን ነው፡፡

በተጨማሪም አዘውትረው በእግረኛ መንገድ መሄድ፣ ያለ አቅጣጫቸው ጭምር እንደሚጓዙና ሌሎችም የትራፊክ ሕጎችን ይጥሳሉ፡፡

አቶ ቢንያም እንደተናገሩት፣ ሌላኛው ችግራቸው ትራፊክ ፖሊስ እንዲያቆሙ ምልክት ሲሰጣቸው ጥሰው ይሄዳሉ፡፡ በአጠቃላይ በትራፊክ ሕግ የተጠቀሱትን ጥፋቶች በአብዛኛው እያጠፉ ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ሔልሜት ማጥለቅ

ሔልሜት (የራስ ቁር) ማጥለቅ ጥቅሙ ለሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ቢሆንም፣ ባለመተግበር ሕጉን እንደሚጥሱ አቶ ቢንያም ይናገራሉ፡፡

እንደሳቸው ገለጻ፣ በዚህም በ2014 ዓ.ም. ብቻ ሔልሜት ባለማጥለቃቸው ምክንያት የተቀጡት 7,540 የሞተር ሳይክሎች አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ በሞተር ሳይክሎች በፍጥነት ወይም ከተፈቀደው የፍጥነት በላይ እንደሚያሽከረክሩና አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩት ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ሔልሜት ያላደረጉ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች በሦስተኛ እርከን በገንዘብ የሚቀጡ መሆኑን፣ ቅጣቱ ከአሽከርካሪው በተጨማሪ አብሮት ያለው ግለሰብ ሔልሜት ካላደረገ ወይም አድርጎ በደንብ ካላሰረ በእርከን ሁለት ቅጣት እስከ 200 ብር ድረስ ይቀጣል ብለዋል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ጂፒኤስ ያላሰሩትን ደግሞ ከወንጀል ጋር ሊያያዝ ስለሚችል በፖሊስ ምርመራ እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል፡፡ የተሰጣቸው የመንቀሳቀሻ ፈቃድና መንጃ ፈቃድ የሌላቸው ከሆነ የሚወሰድባቸውም ዕርምጃ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

አንፀባራቂ ልብስ የመልበስ ግዴታ እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ቢንያም፣ እነዚህም በትኩረት ካልተገበሩ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው አመልክተዋል፡፡ በዚህም በአማካይ ከ500 እስከ 700 የሞተር ሳይክሎች የደንብ ልብስ ባለመልበስ፣ መንጃ ፈቃድ ባለመያዝና በሌሎች ምክንያት በየዓመቱ የሚቀጡ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...