Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹አረንጓዴ አሻራ››

‹‹አረንጓዴ አሻራ››

ቀን:

ሕይወትን ማኖር ተስኖን

ተስፋና ፍቅርን አጥተናል፡፡

ላያችን አምሮና ደምቆ

ውስጣችን እርቃኑን ቆሞዋል፡፡

የዛሬን ታሪክ አሻራ

የሙታን ዐፅም ቀብረናል

የ‹‹ጉቶ›› ሐውልት ወርሰናል

‹‹ዝምታ ዛሬ ነ.ቀ.ዘ›› ¡¡

ወገኔ ምን … ይሻለናል?

            ዋንዛና፣ ዋርካ ተቆርጠው

            ጸጋውን በረሃ ዋጠው፡፡

አዕዋፋት ማረፊያ ናፍቀው

እንደ ሰው ወጡ ተሰደው፡፡

አራዊት እየተገፉ …

ደንብረው ጥለውን ጠፉ

ተፈጥሮ ቁጣዋ በዝቶ …

ቅጣቷ እጅግ በረታ

ብዝኃነት መንምነው ጠፍተው …

ሆነዋል ‹‹የውኃ ሽታ››፡፡

ኩሬዎች ደርቀው ተረሱ

ሐይቆችም በአረም ኮሰሱ፡፡

ወንዞችም አልቀረላቸው …

ጥፋቱ ደርሷል ከነሱ፡፡

‹‹ኩል›› መስለው እንዳልፈሰሱ፡፡

ጥቀርሻ ሆነው ደረሱ፡፡

ንቃ! … ወገኔ

ሀገር ታማለች ገርጥቷል ገጿ

የአካሏ ማድያት ተስፋፍቷል ለምጿ

በእስላም፣ ክርስቲያን በዋቄ-ፈታ

በወንጌል አማኝ በሁሉ ተርታ፣ በሁሉ ቦታ፡፡

መስማት ‹‹ሀራም›› ነው ተፈጥሮ ጠፍታ

ማየት ‹‹ሀጥያት›› ነው ተፈጥሮ ሞታ፡፡

            ንፋ መለከት፣ ጐስም ነጋሪት

ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ክተት ሠራዊት

ደቦ ተጠርቷል … ማይቀርበት

ወጆ ተሠምቷል …

ወፈል ተቀጥሯል … በኢትዮጵያ መሬት

አንድ ጠል ተክለን ሺ-ምናፍስበት

ዘመናችንን በብሩህ ተስፋ የምንዋጅበት!!

ተነስ! … መምህር

ተነስ! … ተማሪ

ስጣት ምላሹን ለኢትዮጵያ ጥሪ፡፡

ተነስ! … ነጋዴ

ተነስ! … ገበሬ

ተፈጥሮ ወድማ የለህም ተስፋ፣

            የለህም ፍሬ!!

ተነስ!! … ወታደር ጀግናው ሣተና

ወትሮም የሀገርህ ጋሻ ነህና፡፡

ተነስ! … ዶክተሩ

ተነስ! … ሐኪሙ

ያየር ለውጥ ነው

በረሃነት ነው የዘመናችን በሽት ስሙ፡፡

ተነስ! … ኦሮሞ

ተነስ! … አማራ ተደ.መ.ር ትግራይ

ችግር አይደለም

ችግኝ ነው ሀገር የሚያሻት ዛሬ

የአዲስ ልጅ ላንተ ማን? ይሰብክልሃል

የሆነው ሁሉ ቀድሞ ይገባሃል፡፡

የአንድነት ቅሬው …. !!

የውበት ጥሪው ይመጥንሃል፡፡

ሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ሶዶ፣ ሲዳሞ

ጉራጌ፣ ኮንሶ፣ ጐፋና ጋሞ፡፡

ቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ ሐረር፣ ሶማሌ

ለጥፋት ቃፊር አትሆኑም ሎሌ፡፡

ይልቅ ተ.ደ.መ.ር …

አኑር አሻራ በጭቃ ቀለም

ትውልድ እንዲድን ሀገር ትታከም፡፡

ሜዳ፣ ተራራ፣ ከተማ ገጠር …!

የሁሉም ሥፍራ፣ የሁሉም መንደር!

በዛፍ በአበባ ይ.ን.ቆ.ጥ.ቆ.ጥ ይመር፡፡!!

ከአድማስ እስከ አድማስ!

ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ … በሁሉም ሥፍራ!

በችግኝ ቀለም

የአንተነትህን አኑር አሻራ፡፡!!

  • አበራ ጀምበሬ
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...