ደራሲው ማርክ ትዌን እኤአ በ1900 ማንሃታን ውስጥ ይኖር በነበረ ጊዜ ተከታዩን ደብዳቤ ለጎረቤቱ ጽፎ ነበር፡፡ ‹‹የተከበሩ እመቤት ኃላፊነቴን ማክበርና መወጣት እንዳለብኝ አውቃለሁ፣ ሆኖም ግን ወንዶች ልጆችን በተመለከተ ደካማና እምነት ቢስ ነኝ እናም የበር ደወሎችን የሚደውሉትን ልጆቹ የደጃፋቸውን ደረጃ ልይ እንዳይሰበሰሱ እንድከለክላቸው ልያሳምነኝ ሞክሯል፡፡ እኔ ግን ልጆቹ ይደሰቱበት ብዬ እተዋቸዋለሁ፡፡ ባለቤቴ ዛሬ ምሽት ስለልጆቹ አቤቱታዋን ስታቀርብልኝ ነበር፡፡ እናም የግዴን ቃል ገብቼላታለሁ፡፡ ሆኖም ግን በጣም ልበቢስ ነኝ፣ ስለሸመገልኩ ደግሞ ኃላፊነቴን የመወጣት ስሜቴ ላልቷል፡፡
- ዮሐናን ካሳ ‹‹የታዋቂ ሰዎች አስቂኝ ደብዳቤዎች እና አባባሎች›› (2004)
********