ስኮትላንዳዊው የጠገበ ሃብታም እንደ ዓይኑ ብሌን የሚንከባከባት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው፡፡ እንደብዙዎቹ ሃብታሞችም ልጁ የናጠጠ ነጋዴ እንድታገባ ይፈልግ ስለነበር ቤሳ ቤስቲኒ የሌለው የነጣ የገረጣ የሃይማኖት ተማሪ ልታገባ እንደሆነ ባሳወቀችው ጊዜ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አቀረበለት፡፡
“ገቢህ ምን ያክል ነው?”
”ምንም ብል ይሻላል፣ጌታዬ፡፡”
”ይህ በእግዚአብሔር እጅ ያለ ነገር ነው፤ ጌታዬ፡፡”
“ልጄን ታድያ በምን ታስተዳድራታለህ? “
“እግዜር ይሰጠኛል፡፡”
“ልጆች ብትወልዱስ ማን ያለብሳቸዋል፤ማንስ ይቀልባቸዋል? “
“ሁሉንም እግዜር ይሸፍነዋል ” አለ ወጣቱ በመተማመን፡፡
ወጣቱ ወደ ቤቱ እንደሄደ የልጅቱ እናት ባለቤቷን “እንዴት አገኘኸው?” ስትል ጠየቀችው፡፡ “ሰውየው ገንዘብ ፤ሥራም ሆነ ተስፋ የለውም፡፡ በዚያ ላይ እኔ እግዚአብሔር ሳልመስለው አልቀረሁም፡፡”
- አረፈዓይኔ ሐጐስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች›› (2005)