Saturday, December 2, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር ደውለው ልማታዊ ወጣቶች ያቀረቡት አቤቱታ በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠው እያሳሰቡ ነው]

  • እየደገፉን ያሉ አንዳንድ ልማታዊ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ ላይ ቅሬታ አቅርበዋል።
  • እኛ ላይ? 
  • አዎ! 
  • ቅሬታቸው ምንድነው? ለምን ለእኛ አላሳወቁንም?
  • የሚሰማቸው ስላላገኙ ነው ቅሬታቸውን ወደ እኛ ይዘው የመጡት። 
  • እስኪ ነገሩን አጣራለሁ ለማንኛውም ቅሬታቸውን ይንገሩኝ?
  • እንደ ልማታዊ ወጣት ለመንግሥት ድጋፍ እያደረግን ቢሆንም በከተማ ውስጥ የመኖሪያ ቤት የምንገነባበት መሬት ልናገኝ አልቻልንም ነው የሚሉት። ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የተፈጸመባቸው እንደሆነ ነው የሚያነሱት።
  • ክቡር ሚኒስትር ከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ እጥረት እንዳለ ያውቃሉ አይደል? ባይሆን ጥያቄያቸውን በሌላ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኝ ብናደርግ አይሻልም?
  • ሌላ መንገድ ማለት?
  • ባዶ የሆኑ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ካሉ ፈልገን እንዲያገኙ ማድረግ እንችላለን።
  • ኮንዶሚኒየም ቤትማ በራሳቸው መከራየት ይችላሉ ወይም …
  • ወይም ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ወይም ሊገዙ ይችላሉ።
  • እንደዚያ ማድረግ እየቻሉ ለምን በእኛ ላይ ቅሬታ ያቀርባሉ ታዲያ? 
  • ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ መሬት እንዲሰጣቸው ጠይቀው በመከልከላቸው አልኩኝ እኮ፣ አልሰሙኝም?
  • ክቡር ሚኒስትር ኮንዶሚኒየም ቤት መከራየት ወይም መግዛት እየቻሉ መሬት እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው በራሱ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? 
  • እንዴት? ድጋፍ የሚያደርጉልን ልማታዊ ወጣቶች ናቸው እያልኩኝ አይደለም እንዴ? 
  • እህ… እንደዚያ ነው?
  • እንዲያውም እነሱ ሳይጠይቁ ነበር መሬት እንዲያገኙ ማድረግ የነበረባችሁ። ስለዚህ በአስቸኳይ አስተናግዷቸው።
  • ክቡር ሚኒስትር ጥያቄውን እናስተናግዳለን ነገር ግን
  • ግን የሚባል አልቀበልም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ለምን መሰልዎት…?
  • እህ…
  • በአሁኑ ወቅት ያለውን መሬት ወረራ ለመከላከል ብለን የመሬት ጥያቄዎችን እያስተናገድን አይደለም። 
  • በልዩ ሁኔታ የምታስተናግዱት እንዳለ ሰምቻለሁ።
  • የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ጥያቄ ብቻ ነው በልዩ ሁኔታ እያስተናገድን ያለነው።
  • ቢሆንም እነሱንም በዚሁ መንገድ ማስተናገድ ትችላላችሁ፣ ከላይ የወረደ ትዕዛዝ ነው!
  • ልማታዊ ወጣቶች ናቸው አላሉም እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
  • አዎ፣ ልክ ነው።
  • ታዲያ አርሶ አደሮች ካልሆኑ ምን ብለን እናስተናግዳቸዋለን?
  • የአርሶ አደር ልጆች። 

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ አማካሪያቸው ፊቱ በፈገግታ ተሞሎቶ እንኳን ደስ አለዎት ክቡር ሚኒስትር እያለ ወደ ቢሯቸው ገባ]

  • ፊትህ በፈገግታ ደምቋል፣ ምን አዲስ ነገር አለ? 
  • በጣም ደስ የሚል ነገር ነው የሰማነው ክቡር ሚኒስትር። እንኳን ደስ አለዎት፡፡
  • ምን ሰምተህ ነው? 
  • ውርጅብኙ ሲበዛባቸው ያቀረቡትን ጥሪ ሰምቼ ነው። 
  • ጁንታዎቹን ማለትህ ነው? አዲስ ነገር ጥሪ አቀረቡ እንዴ? 
  • አልሰሙም እንዴ? ጡጫው ሲበዛባቸው እኮ 
  • የአፍሪካ ኅብረትን አደራዳሪነት እንቀበላለን አሉ፡፡ 
  • አይ አንተ! ቀድሞውንስ መቼ የአፍሪካ ኅብረት አያደራድረንም አሉ? 
  • የአፍሪካ ኅብረትን ሲያንቋሽሹ አልነበረም አንዴ? አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ የውጭ መንግሥታትም የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነትን መቀበሉን በማድነቅ መግለጫ ማውጣታቸውን አይቻለሁ። 
  • ሆነ ብለው እያደናገሩ ነው እንጂ እስካሁን ድረስ ሲያደራድረን የቆየው የአፍሪካ ኅብረት ነው። 
  • ታዲያ አዲሱ ነገር ምንድነው? 
  • ምንም አዲስ ነገር የለም።
  • ምን የተለየ ነገር የለም? 
  • አዎ። በፊትም ቢሆን የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነትን አለመቀበል ችግር እንደሚያመጣባቸው ስለሚያውቁ ኅብረቱን አንቀበልም አላሉም። ኅብረቱ የሾማቸው አደራዳሪ ላይ ግን የማጥላላት ዘመቻ ከመክፈት ባለፈ እርሳቸውን በአደራዳሪነት አንቀበልም ብለዋል።
  • አሁን ግን ይህንን አቋማቸውን የቀየሩ ይመስለኛል። አይደል ክቡር ሚኒስትር? 
  • ምንም ዓይነት የአቋም ለውጥ አላደረጉም።
  • በናይጄሪያዊው ሰውዬ ላይ የነበራቸው አቋምም አልተቀየረም? 
  • በፍጹም! ያወጡት መግለጫ ምን መሰለህ የሚለው?
  • እሺ… እየሰማሁ ነው ይቀጥሉ ክቡር ሚኒስትር?
  • በአፍሪካ ኅብረት የሚመራ የሠላም ሒደትን እንቀበላለን። ኅብረቱ ሁለቱም ወገኖች ተስማምተው የተቀበሉትን አደራዳሪ መሾም አለበት ነው የሚለው።
  • ለምንድነው ታዲያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጁንታውን እያወደሰ ያለው? 
  • መንግሥት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን ገፋ በማለት ዘመቻ ለመክፈት ስለፈለጉ ነው።
  • መንግሥት በማንኛውም ቦታና ጊዜ ያለ ቅደመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለአፍሪካ ኅብረት ጥሪ ማቅረቡን አያውቁም እንዴ? 
  • ያውቃሉ! 
  • ታዲያ ለምን ጁንታው ይህንን እንዲቀበል ጥሪ አላቀረቡም? 
  • ጁንታው የሚፈልገውን ነገር የያዘ ባለመሆኑ ይመስለኛል። 
  • ጁንታው የሚፈልገው ምንድነው?
  • ቅድመ ሁኔታ! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...

ሀብቱንና ትርፉን እያሳደገ የቀጠለው አዋሽ ባንክ

አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[ጉባዔው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ክቡር ሚኒስትሩን ለመጠየቅና ምላሽና ማብራሪያቸውን ለማድመጥ ተሰብስቧል። የጉባዔው አባላትም ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎቻቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር፣ ይህ ጉባዔ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በመካከላችን ስለተገኙ አመሰግናለሁ። ክቡር ሚኒስትር፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የብሪክስ አባል እንድትሆን የሰጡት በሳል አመራር የሚደነቅ ነው። አገራችን...