Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ለተከታታይ አሥራ አንድ ቀናት ቴአትር ሊያሳይ ነው

አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ለተከታታይ አሥራ አንድ ቀናት ቴአትር ሊያሳይ ነው

ቀን:

ለተከታታይ ሁለት ዓመታት በእድሳት ላይ የነበረው አንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ከመስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አሥራ አንድ ቀናት የተለያዩ ቴአትሮችን እንደሚያሳይ አስታውቋል፡፡

በመክፈቻው ዕለት መስከረም 3 ቀን ‹‹የመንግሥት ሥራ›› የተሰኘው በተሻለ ወርቁ የተደረሰው ቴአትር ለታዳሚያን የሚቀርብ ሲሆን በተከታታይ ቀናትም ለተመልካች የሚቀርቡ ቴአትሮች አዳዲስና ከዚህ ቀደም ሲታዩ የቆዩ ናቸው፡፡

በተከታታይ ቀናት አሉ፣ ላጤው ባለትዳር፣ የእኛ ሰፈር፣ ጋዜጠኛው፣ ክሊዮፓትራ፣ የጉድ ቀን፣ ከመጋረጃ ጀርባ፣ የሌሊት ሙሽሮችና ነገሩ አያልቅ የተሰኙ ቴአትሮችም ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በእነዚህ ቀናት የተለያዩ ቴአትሮች የሚቀርቡ ሲሆን፣ በተለይ ከመጋረጃ ጀርባና ጉድ ቀን የተሰኙት ቴአትሮች ይደገማሉ ተብሏል፡፡

ታሪካዊና ጥንታዊ እንደሆነ የሚተረክለት የሀገር ፍቅር ቴአትር የተመሠረተው ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ከመውረሩ አንድ ዓመት በፊት በ1927 ዓ.ም. ነበር፡፡ የብዙ አንጋፋ አርቲስቶች መፍለቂያ ሀገር ፍቅር በአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሆኑ ጭምር ይተረክለታል፡፡

ሀገር ፍቅር ቴአትር ሐምሌ 11 ቀን 1927 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ማኅበር ተብሎ የተመሠረተ ሲሆን ማኅበሩ በመዲናው ያለውን ሕዝብ ለአርበኝነት ዓላማ ለማነሳሳት የተቋቋመ ነው፡፡ በወቅቱ የነበሩት አንጋፋና ታዋቂዎች መካከል ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ወልደ ዮሐንስ ጊዮርጊስ፣ ዮፍታሔ ንጉሤና ሌሎች ባለ አንደበተ ባለሙያዎች ዲስኩር ያስሙበት ጭምር ነው፡፡

ወራሪው ፋሽስት ጣሊያን ከአምስት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ለቆ ከወጣ በኋላ ዘርፈ ብዙ ለውጦችንም አስተናግዷል፡፡ የቴአትር ቤቱ ታላላቅ የጥበብ ፈርጦች መካከል አበራ ደስታ፣ ዘነበች ታደሰ፣ የሺ ተክለ ወልደ፣ ሙናዬ መንበሩ፣ በላይነሽ አመዴ፣ በቀለ ወልደ ፃድቅ፣ ሌሎችም አንጋፋ ባለሙያዎች ስማቸው ይነሳል፡፡

ከተጠቀሱት የጥበብ ፈርጦች በተጨማሪ፣ በሁለገብ ከያኒነታቸው እስከአሁን ዘመን ድረስ መተኪያ ያልተገኘላቸው ለሀገር ፍቅር ቴአትር ብቻ ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያ ቴአትር ዕድገት ምሰሶ ከሆኑ ባለሙያዎች ውስጥ ኢዩኤል ዮሐንስ፣ ማቴዎስ በቀለና መላኩ አሻግሬ በጉልህ ይነሳሉ፡፡

እነዚህ ሁሉ ዘመን አይሽሬ ባለሙያዎችን ያፈራው የሀገር ፍቅር ቴአትር ሕንፃ ዕድሳት ቢያስፈልገውም ለረዥም ዓመታት ሳይታደስ መቆየቱ ይነገራል፡፡

በ1990ዎቹ መገባደጃ ቴአትር ቤቱ አሁን ያለበትን ቅርፅ ከያዘ በኋላ ለዓመታት ዕድሳት እንዳልተደረገለት ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዱልከሪም ጀማል መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ከ20 ዓመታትና ከዚያ በፊት ሲገለገሉበት የቆየውን የመድረክ መብራቶች፣ የመድረክ በስተጀርባ መገልገያዎችና ሌሎችም ቁሶች የቆዩና ያረጁ በመሆናቸው መታደስ ይገባቸው ነበር፡፡

የቴአትር ቤቱ መጋረጃዎች፣ ወንበሮች፣ መቀመጫዎች ያረጁና የቆሸሹ እንደነበሩ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ለዕይታም ሆነ ለተመልካቾች ምቹ አልነበሩም፡፡ አሁን በዓለም ላይ ያለውን ቴአትር ቤት ደረጃ መሥራት ባይቻል እንኳን፣ በተወሰነ ደረጃ ለባለሙያዎችና ለተመልካች ለዕይታና ለምቾችትም የተሻለ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

ከታኅሣሥ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የቴአትር ቤቱ ዕድሳት መጀመሩን፣ ዕድሳቱ ያካተተው ሙሉ ግቢውን መሆኑን በዋናነነት ዋና የቴአትር ማሳያ የሆነውን ትልቁ አዳራሽን ወንበር፣ መጋረጃ፣ ወለል፣ የመብራትና የድምፅ ግብዓቶችን ዘመናዊ በማድረግ ታድሷል፡፡

የሀገር ፍቅር ቴአትር የዕድሳት ፕሮጀክቱን የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ዕድሳቱ የተከናወነው በኮንስትራክሽን ቢሮ አማካይነት ነው፡፡

በአሁን ጊዜ በቴአትር ቤቱ የቴአትር፣ የሙዚቃና ውዝዋዜ ባለሙያዎች ጨምሮ ከ135 በላይ ቋሚ ሠራተኞች አሉት፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...