አዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የአገሪቱ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላቸውን መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ከፈጸሙ በኋላ የአስተዳደራቸውን ዋና ዋና ትኩረቶችን በማስመልከት ባሰሙት ዲስኩር ላይ የተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚያከናውኑትን ተግባር እንደሚቀጥሉ ያወሱት ሩቶ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያና በታላላቅ ሐይቆች ቀጣና ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር ማከናወናቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ ኬንያታ የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል መስማማታቸውንም ጠቅሰዋል።