Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ሕፃናት ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ ሆነዋል ተባለ

በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ሕፃናት ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ ሆነዋል ተባለ

ቀን:

በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሕፃናት ለጉልበት ብዝበዛ ጥቃቶችና ለድርቅ፣ ለጎርፍና ለረሃብ መጋለጣቸውን ‹የአፍሪካ ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም› አስታወቀ፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ 35 አገሮች ውስጥ የሚገኙ 490 ሚሊዮን ሕፃናት ለከፋ የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያስከትሉት ችግሮች የተጋለጡ መሆናቸውን፣ ጳጉሜን 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ ማዕከል ባደረጉት ዘጠነኛው ዓለም አቀፍ  ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡

በአፍሪካ ቢያንስ 11 ሚሊዮን ሕፃናት በድርቅና በጎርፍ በአስከፊ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የምግብ ዋስትና ዕጦት እንዳጋጠማቸው፣ የፎረሙ ዋና ዳይሬክተር ጆአን ኒያንዩኪ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሕፃናቱ ሕይወት፣ በጤና እና ትምህርት ዕጦትና በደኅንነት መብቶቻቸው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት፣ በቅርቡ በተደረገው ጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ 45 ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ሥጋት ካለባቸው አገሮች 35ቱ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህም ከሰሃራ በታች ያሉ አገሮች በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በርካታ ሥራዎችን መሠራት እንዳለባቸው ያሳያል ብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ሕዝብ ግማሹ ከ20 ዓመት በታች መሆኑ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፣ በአስከፊ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ቀዳሚ ተጎጂዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡›› በአገሮቹ የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በመከሰታቸው፣ የረዥም ጊዜ ተፅዕኖ በሆነው የድህነት መጨመር፣ የኢንቨስትመንት እጥረትና የመሠረተ ልማት በመሟላቱ ለችግር የተጋለጡ ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

በጥናቱ መሠረት ቻድ፣ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራና የኮንጎ ሪፐብሊክ የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ለመቋቋም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

አንጎላ፣ ሌሴቶ፣ ማዳጋስጋር፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ታንዛኒያና ዚምባቡዌ በድርቅና በጎርፍ ሳቢያ የምግብ ዋስትና ዕጦት ችግር ያለባቸው መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በእነዚህ አገሮች ሕፃናትን ጨምሮ ከ11 ሚሊዮን ለችግር የተጋለጡ መሆኑን የገለጹት ጆአን (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ጥናት እንዳመለከተው እ.ኤ.አ. 2100 የአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት በምዕራብ አፍሪካ ብቻ ሕፃናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በ37 በመቶ ይጨምራል ብለዋል፡፡

በዚሁ ዓመት በመካከለኛው አፍሪካ ደግሞ የሕፃናት የተመጣጠነ የምግብ እጥረት በ25 በመቶ ሊጨምር እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

አፍሪካ የተሟላ ዕድገት ካገኘች እ.ኤ.አ. በ2050 ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህዳሴ ሊያግዙ የሚችሉ አንድ ቢሊዮን ሕፃናትና ወጣቶች መኖሪያ እንደምትሆን ይገልጻሉ፡፡

ነገር ግን በአየር ንብረት ለውጥ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ምክንያት የሥራ፣ ምርታማነትና ዕድገት ሊቀንስ እንደሚችል የአፍሪካ ፖሊሲ ፎረም ባለአደራ ሰብሳቢ ሚስስ ግራሳ ማሼል ተናግረዋል፡፡

ባለአደራ ሰብሳቢዋ እንዳስረዱት፣ በአፍሪካ ለሕፃናትና ወጣቶች ይውል የነበረው መዋለ ንዋይ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ሊተገበር ይችላል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው የቀውስ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ሕፃናትና ወጣቶች መሆናቸውንና፣ ይህም ለአሥር ዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የአፍሪካ ሕፃናት ለተለያዩ ችግሮች እንዳይጋለጡ መሠራት አለበት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራች እንደምትገኝ፣ ነገር ግን አሁንም ቀሪ ሥራዎች እንደሚቀሩ ገልጸዋል፡፡

ለዘጠነኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፖሊሲ ፎረም ጉባዔ ላይ የሕፃናት መብት ተሟጋቾች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ የአፍሪካ ኅብረትና የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ባለሥልጣኖችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...