ዕንቁጣጣሽ አንተ ስጦታህ የበዛ፣
ለሰው መታሰቢያ ውበት የምትገዛ፡፡
በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤
ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን፡፡
….
ፍየሎች ይዘላሉ ቅጠል ይበጥሱ፤
ከተሰደዱበት ወፎች ይመለሱ፡፡
ይልቀሙት እህሉን፤ ይስሩ ቤታቸውን፤
ይስፈሩበት ዛፉን፡፡
የደስ ደስ ያሰሙ ንቦች ይራኮቱ፤
ይንጠራሩ አበቦች ይንቁ ይከፈቱ፡፡
አንበሳና ግልገል በውስጡ ይፈንጩ፤
ከብቶች ሳሩን ይንጩ፡፡
ሕጻናት ይሩጡ ይሳቁ ይንጫጩ፤
ከብቶች ሳሩን ይንጩ፡፡
ሕፃናት ይሩጡ ይሳቁ ይንጫጩ፤…
ዐደይ አበባ ነህ የመስቀል ደመራ፤
ጠረንህ አልባብ ነው አየርህ የጠራ፡፡
- ገብረ ክርስቶስ ደስታ ‹‹መንገድ ስጡኝ ሰፊ››