Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስ ከሱዳኑ አል ሒላል ጋር ዛሬ በአዲሱ ዓመት መባቻ ይጫወታል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሱዳኑ አል ሒላል ጋር ዛሬ በአዲሱ ዓመት መባቻ ይጫወታል

ቀን:

በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ እሑድ መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲሱ ዓመት መባቻ ከሱዳኑ አል ሒላል ጋር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

 አል ሒላል ባለፈው ሳምንት ከፀጥታ ሥጋት ጋር በተገናኘ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጨዋታው በገለልተኛ አገር እንዲሆን ጠይቆ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ብዙ ጊዜ የውጭ ዜግነት ባላቸው አሠልጣኞች በመሠልጠን የሚታወቀው  ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከዓመታት በኋላ በአገር ውስጥ አሠልጣኞች ያውም በቀድሞው የክለቡ ተጫዋች ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ ነው ጨዋታውን የሚያደርገው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግም ሆነ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ካፍ የውድድር ቅርፁን (ፎርማት) በአዲስ መልክ ከቀየረ በኋላ፣ በመድረኩ ውጤታማ ጉዞ በማድረግ ከአገሪቱ ክለቦች የመጀመሪያ ያደርገዋል፡፡ የውድድር ዓይነቱ ከመቀየሩ በፊት ግን ኢትዮጵያ መድን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ጥሩ ደረጃ የደረሰበት አጋጣሚ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የዓምናው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለዚህ ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ከቀናት በፊት ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዴሚ፣ ከሌላው የሱዳን ክለብ ከሆነው አልሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 3 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ የሱዳኑ አልሜሪክ ቀደም ብሎ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ቀደም ሲል የባህር ዳሩ ጨዋታ በገለልተኛ አገር ሜዳ እንዲሆንለት ለካፍ ጥያቄ ያቀረበው የሱዳኑ አል ሒላል፣ ጥያቄው ተቀባይነት አለማግኘቱን ካወቀ በኋላ አዲስ አበባ የገባው ሐሙስ ጳጉሜን 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...