በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ማገርሸቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ
ክርስቲያን ሰሞኑን “ለሚመለከታቸው ወገኖች” በሙሉ ብላ ካስተላለፈችው
የተማፅኖ መልዕክት የተወሰደ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ በግሏ እንዲሁም ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር በመሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት አስመልክቶ በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዋን ስታቀርብ መቆየቷን አስታውሳ፣ አሁንም በአካባቢው ጦርነት ዳግም ማገርሸቱን በማስተዋላችን እጅጉን አሳዝኖናል ብላለች። እስካሁን በነበረው ጦርነት በርካቶች ሕይወታቸው መቀጠፉን፣ በርካታ ንብረትም መውደሙን፣ ጦርነቱ ትቷቸው ባለፉ ጠባሳዎች ምክንያት በተለይ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና ዐቅመ ደካሞች ለከፍተኛ የኑሮ ቀውስ መዳረጋቸው አሳሳቢነቱን ጠቅሳለች። ‹‹ሕዝባችን በኑሮ ውድነት ጫና ውስጥ እየታገለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በማናቸውም ወገኖች የኃይል አማራጮችን መውሰድ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው›› ስትልም አክላለች፡፡