Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፋሲል ከነማ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጉዞውን ዓርብ ይጀምራል

ፋሲል ከነማ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጉዞውን ዓርብ ይጀምራል

ቀን:

ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው ፋሲል ከነማ፣ ከነገ በስቲያ ዓርብ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ይጫወታል፡፡ ፋሰል ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

በአሠልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ የሚሠለጥነው ፋሲል ከነማ፣ በአኅጉራዊ ውድድሮች ላይ ልምድ ካላቸው ክለቦች አንዱ ቢሆንም፣ እስካሁን በመድረኩ ይህ ነው የሚባል ውጤት ማስመዝገብ ሳይችል ቆይቷል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በዘንድሮ ውድድር ላይ ቢያንስ ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን ጠንካራ ዝግጅት ማድረጉን የክለቡ አሠልጣኝና ደጋፊዎቹ ይናገራሉ፡፡

ፋሲል ከነማ ባለፈው የውድድር ዓመት በአሠልጣኝ ሥዩም ከበደ እየተመራ በመጀመሪያው ዙር መሰናበቱ አይዘነጋም፡፡ በመድረኩ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በስተቀር ፋሲል ከነማ ጨምሮ የአገሪቱ ክለቦች ይህ ነው የሚባል ውጤት እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፋሲል ከነማ ዓርብ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር የሚደርገው ጨዋታ ከወዲሁ እንዲጠበቅ አድርገታል፡፡          

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...